Fana: At a Speed of Life!

የፌደራል ፖሊስ አመራሮችና አባላት ደም ለገሱ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 4፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ)የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አመራሮችና አባላት “ደማችን ለሰራዊታችን” በሚል መሪ ቃል ደም ለገሱ፡፡

በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል ዘርፍ የምስራቅ ኢትዮጵያ ፈጥኖ ደራሽ ዳይሬክቶሬት አመራርና አባላት ወንጀልን ከመከላከል ተግባራቸው ጎን ለጎን አሸባሪውን የጁንታ ቡድን ለመመከት በግዳጅ ላይ ለሚገኙ አካላት ደም ለግሰዋል፡፡

“ደማችን ለሰራዊታችን” በሚል መሪ ቃል ድሬዳዋ ከሚገኘዉ የብሄራዊ ደም ባንክ ጋር በመተባበር ደም የለገሱት የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አመራርና አባላቱ የሃገር ክብርና ሉዓላዊነትን ለመዳፈር የሚንቀሳቀሱ የአሸባሪው ህወሓት ቡድን ተላላኪዎችን እኩይ ድርጊት በመመከት ለዜጎች ሰላምና የህግ የበላይነት መከበር እስከ ህይወት መስዋዕትነት ለመክፈል የላቀ ዝግጁነት እንዳላቸው ገልፀዋል፡፡

የደም ልገሳው የሃገር ህልውናን ለማስከበር በተለያዩ ግንባሮች ተሰማርተው ለሚገኙ የሃገር መከላከያ ሰራዊት፣ የፌዴራል ፖሊስና ሌሎች የፀጥታ አካላት መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡

አመራርና አባላቱ በተሰማሩበት የግዳጅ ቀጠና ከማህበረሰቡና ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት ለአካባቢው ሰላምና ፀጥታ መከበር ጉልህ አስተዋፅኦ በማድረግ ፖሊሳዊ ተልዕኳቸውን እየተወጡ እንደሚገኙ ከፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.