Fana: At a Speed of Life!

የፌደራል ፖሊስ የሎጀስቲክስ ዋና መምሪያን ህንፃ አስመረቀ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የሎጀስቲክስ ዋና መምሪያን ህንፃ አስመረቀ።

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አስተዳደር ልማት ዘርፍ ኃላፊ ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል ነቢዩ ዳኜ፥ የተመረቀው የሎጀስቲክስ ዋና መምሪያ ህንፃ በፌደራል ፖሊስ ተቋም ውስጥ የእድገት ምልክት ሆኖ የሚያገለግል፣ የሪፎርማችን ውጤት የሆነና ለሠራዊቱ ትልቅ አገልግሎት የሚሰጥ ይሆናል ብለዋል፡፡

የፌደራል ፖሊስ አስተዳደር ልማት ዘርፍ እንደ አንድ የፖሊስ ሰራዊት ተቋም የሎጂስቲክስ ስራን በማደራጀት ለፖሊሳዊ ዘመቻ የጀርባ አጥንት ሆኖ የሚያገለግል ጠንካራ የስንቅ፣ የትጥቅና ልዩ ልዩ አቅርቦትን የሚያፋጥን ተቋም አስፈላጊ በመሆኑ ህንፃ ማስገንባቱን ተናግረዋል፡፡

የአስተዳደር ልማት ዘርፍ በ2013 እና 2014 በጀት ዓመት ለፖሊስ ግዳጅ መፈፀሚያ የሚያገለግሉ ልዩ ልዩ መሳሪያዎች የማቅረብና የማስታጠቅ ስራዎች በስፋት የተከናወኑበት መሆኑን ጠቁመው፥ በቴክኖሎጂ ስራዎች የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ወደ አዲስ ምዕራፍ የተሸጋገረበት፣ ዲጂታል ራዲዮን ስራ ላይ ያዋለበት እና በመዲናችን ሰላምና ደህንነትን ለማረጋገጥ አጋዥ የሆኑ የቴክኖሎጂ ኦፕሬሽን ማዕከሎች የተፈጠሩበት እንዲሁም አሰራሮቻችንን ለማዘመን የሚያግዙ ፈጠራዎች የተከናወኑበት በጀት ዓመት ነው ሲሉም ገልጸዋል፡፡

ተቋሙ በሪፎርም ስራዎች፣ በስትራቴጂ፣ በመዋቅር፣ በአሰራር ረገድ ያከናወናቸው ተግባራት ሲመዘኑ ስር-ነቀል ሪፎርም እንደ ተካሄደ ተደርጎ የሚወሰድ መሆኑ ተመልክቷል።

ዘርፉ ከነበረበት በችግር ወጥቶ የተሻለ የመፈፀም አቅም እንዲፈጥር አስችሎታል ማለታቸውን ከፌደራል ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.