Fana: At a Speed of Life!

የፌዴራል መንግስት የመሬት ይዞታ አያያዝን ለማዘመን የሚያስችል ስራ እየተሰራ ነው

አዲስ አበባ፣ ነሀሴ 25፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ የመሬት ባንክና ልማት ኮርፖሬሽንና የኢትዮጵያ ጂኦስፓሻል ኢንፎርሜሽን ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር የፌዴራል መንግስት
የመሬት ይዞታን የሚያዘምን ስራ በማከናወን ላይ መሆኑ ተገልጿል።

ለ311 ተቋማት መረጃ ተደራጅቶ ካርታ መዘጋጀቱም ተጠቁሟል።

ሶስት የስትራተጂ አቅጣጫዎችን በመያዝ የተቋቋመው የኢትዮጵያ የመሬት ባንክና ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር ወይዘሪት ሌንሳ መኮንን፥ መሬት ለሚፈለገው ልማት እንዲውል ዘመናዊ የመረጃ አያያዝ ስርዓት እየተፈጠረ መሆኑን ገልጸዋል።

ኮርፖሬሽኑ የፌዴራል መንግስት ተቋማትን የመሬት ይዞታ መረጃ በአንድ ቋት በማሰባሰብ ለውሳኔ አሰጣጥ በሚያስችል መልኩ እያዘጋጀ መሆኑን ተናግረዋል።

መረጃውን በማደራጀት የአዋጭነት ጥናት በማድረግና በመተንተን መሬትን ማልማትና ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታውን ለማሳደግ ጥረት በመደረግ ላይ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።

የተቋማቱን የመሬት መረጃ ማደራጀት፣ የአዋጭነት ጥናት ማጥናትና ልማት ላይ መዋሉን ማረጋገጥ የኮርፖሬሽኑ ስትራተጂክ አቅጣጫ መሆኑን መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.