Fana: At a Speed of Life!

የፌዴራል ፖሊስ ማኔጅመንት አባላት በህክምና ላይ የሚገኙ የፖሊስ አባላትን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ሚያዝያ 15፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በጉብኝቱ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገብረሚካኤልን ጨምሮ ሌሎች የተቋሙ ማኔጅመንት አባላት እንዲሁም የሆስፒታሉ ከፍተኛ አመራሮችና የጤና ባለሙያዎች ተሳትፈዋል፡፡

ከሸኔና ከህወሓት አሸባሪ ቡድኖች ጋር በተለያዩ ግንባሮች በጀግንነት ሲፋለሙ የአካል ጉዳት ደርሶባቸው በሆስፒታሉ በህክምና ላይ የሚገኙት የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ አባላት፥ የአፋር ፖሊስ ልዩ ኃይል አባላት፣ የአማራ ክልል ልዩ ኃይል አባላት፣ የኦሮሚያ ክልል ፖሊስና ልዩ ኃይል አባላት እንዲሁም የሌሎች የክልሎች የፖሊስ አባላት ይገኙበታል።

የማኔጅመንት አባላቱ ጉዳት የደረሰባቸውን የፖሊስ አባላት ለሀገር ሰላምና ደህንነት መከበር ሲሉ ለከፈሉት መስዋዕትነት አመስግነው፥ የፋሲካን በዓል አስመልክቶ ያዘጋጁትን የገንዘብ ስጦታ በተቋሙ ስም ጉዳት ለደረሰባችው ለሁሉም የፖሊስ አባላት አበርክተዋል።

ታካሚ የፖሊስ አባለቱም በተደረገው ጉብኝትና ስጦታ መደሰታቸውን ገልፀው የደረሰባቸው የአካል ጉዳት የሀገራችንን ሰላምና የሕዝባችንን ደህንነት ለመጠበቅ ስለሆነ የከፈሉት መስዋዕትነት እንደሚያኮራቸው ተናግረዋል።

አያይዘውም ጉብኝቱና ስጦታው ከፍተኛ ደስታና የመንፈስ ጥንካሬ እንደፈጠረላቸው መናገራቸውን ከፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.