Fana: At a Speed of Life!

የፌዴሬሽን ምክር ቤት ለ125ኛው የአድዋ ድል በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፈ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 22፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የፌዴሬሽን ምክር ቤት ለ125ኛው የአድዋ ድል በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፏል፡፡

በፌዴሬሽን ምክር ቤት የህዝብ ግንኙነትና የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት የዘንድሮው 125ኛው በዓል “አድዋ ኅብረብሄራዊ አንድነት ዓርማ” በሚል መሪ ሀሳብ እየተከበረ ይገኛል።

ምክር ቤቱ “ለሀገር ነፃነት ከፍተኛ መስዋዕትነት ከከፈሉት አያቶቻችን ጀግንነትና ቆራጥነት እየተማርንና የአድዋን የመደመር እሳቤ ይዘን በዓሉን በማክበርና በመዘከር በሀገራችን የተጀመሩትን ሁለንተናዊ የብልጽግና መንገዶቻችን በማስቀጠል፤ ዘላቂ ሠላም፣ ዋስትና ያለው ዴሞክራሲ እንዲሰፍን፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ዕድገታችን እንዲፋጠን፣ በመፈቃቀድ ላይ የተመሰረተ አንድነት ስር እንዲሰድ፣ ከአድዋ ድል የተማርነውን ሕብር ብሄራዊ አንድነት በተግባር ማሳየት አለብን” ብሏል።

“ኢትዮጵያ የጥቁር አፍሪካውያን፣ የነፃነት ፋና ወጊ ናት፣ ኢትዮጵያ በቅኝ ግዛት ያልተገዛች ብቸኛዋ አፍሪካዊት ሀገርና ለአፍሪካውያን የነፃነት ተምሳሌት ናት፤ ሁሉም የዓለም ጥቁር ሕዝቦች ነፃ እንዲወጡ ከፍተኛ ሚና የተጫወተች በመሆኗም ሁልጊዜም በታሪክ ስትወሳ” ትኖራለችም ነው ያለው።

“ድሉ ለኢትዮጵያ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ሕዝቦች የነፃነታችን ብቻ ሳይሆን የአንድነታችን ድር እና ማግ ነው፣ የብዝኃነታችንና የጥንካሬያችን ምንጭ መሆኑን ያሳየንበት ጭምር ነውም” ብሏል።

“በመሆኑም አያቶቻችንና ቅድመ አያቶቻችን በፈጸሙት አኩሪ ገድል በተገኘው ነፃነት እኛ የዛሬ ትውልድ በኩራትና በነጻነት በዓለም አደባባዮች ቀና ብለን እንድንቆምና ሰንደቅ ዓላማችን ከፍ ብሎ በኩራት እንዲውለበለብ ስላደረጉ ሁልጊዜም በታላቅ ክብርና ምስጋና እናወድሳቸዋለን፤ እንዘክራቸዋለን” ብሏል ምክር ቤቱ፡፡

በዓሉ ወርቃማ ታሪካቸውንም ለመጠበቅና ለመንከባከብ ቃላችንን የምናድስበት ይሆናልም ነው ያለው ምክር ቤቱ በመልዕክቱ፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.