Fana: At a Speed of Life!

የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባኤ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን መልዕክት ለአውሮፓ ህብረት የስራ ሃላፊዎች አደረሱ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 3 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባኤ አደም ፋራህ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን መልዕክት ለአውሮፓ ህብረት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ቻርለስ ሚሼል እና ለአውሮፓ ኮሚሽን ፕሬዚዳንት ዩርሱላ ቮን ደር ላየን አድርሰዋል፡፡

አፈጉባኤው ከአውሮፓ ህብረት አመራሮች ጋር ኢትዮጵያ ሰላማዊ፣ ነፃ፣ እና ፍትሓዊ ምርጫ ለማድረግ እያደረገች ያለው ጥረት፣ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ድርድር፣ በትግራይ እየተደረገ ያለው የሰብአዊ ድጋፎችና ሌሎች የጋራ ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡

በዚህ ወቅትም የአውሮፓ ህብረት የስራ ሃላፊዎች በትግራይ ክልል ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች የሚደረገው ድጋፍ በአግባቡ እንዲደርሳቸው የሚደረገው ጥረት ይበልጥ መጠናከር እንዳለበት ገልጸዋል፡፡

የስራ ሃላፊዎች በትግራይ የተፈጸመውን የሰብአዊ መብት ጥሰት አስመልክቶ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ከመንግስታቱ ድርጅት የሰብአዊ መብት ከፍተኛ ኮሚሽን ጋር በጋራ የጀመረው የምርመራ ሂደት የሚበረታታ ነው ማለታቸውን የምክር ቤቱ መረጃ ያመለክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.