Fana: At a Speed of Life!

የፍልቱ ወረዳ የእሳት አደጋ መከላከያ ባለመኖሩ መንግሥት ድጋፍ እንዲያደረግ ተጠየቀ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 30፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) የፍልቱ ወረዳ የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዴቅ ኢብራሂም የፍልቱ ወረዳ የእሳት አደጋ መከላከያ ባለመኖሩንና እሳት ማጥፋት የሚቻልበት መንገድ ስለሌለ መንግሥት ለወረዳው ድጋፍ እንዲያደረግ ጠየቁ።

የሊባን ዞን ፖሊስ አዛዥና በፍልቱ ወረዳ የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ጽ/ት ቤት ኃላፊ ትናንት ማታ በፍልቱ ከተማ በተከሰተው የእሳት ቃጠሎ ጉዳት የደረሰባቸው አካባቢዎች ተዘዋውሮ ተመልክቷል።

በከተማዋ ትናንት ከምሽቱ 12 ሰዓት ላይ በንግድ ገበያ ላይ በተከሰተው ከፍተኛ የእሳት ቃጠሎ፣ በንብረት ላይ ከፍተኛ ኪሳራ ማስከተሉና በሰባት ግለሰቦች ላይ የመቆሰል ጉዳት ማድረሱን የሊባን ዞን ፖሊስ መመሪያ ዋና አዛዥ ኮማንደር ኢብራሂም ከሊፍ ገልፀዋል።

የሊባን ዞን ፖሊስ ኮሚሽነር ኮማንደር ኢብራሂም ከሊፍ አህመድ ÷ እሳቱ በኤሌክትሪክ መስመሮች እና በነዳጅ ማደያ ላይ በተፈጠረው ችግር መከሰቱንና በተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችና በመንግስት የጋራ ርብርብ መጥፋቱን ተናግረዋል።

በሌላ በኩል የፍልቱ ወረዳ የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዴቅ ኢብራሂም የፍልቱ ወረዳ የእሳት አደጋ መከላከያ ባለመኖሩ መንግሥት ለወረዳው የእሳት አደጋ መከላከያ ድጋፍ እንዲያደረግ መጠየቃቸውን ከሶማሊ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.