Fana: At a Speed of Life!

የፍትህ ስርዓቱን ማረጋገጥ ካልተቻለ ዘላቂ ሰላምም ሆነ እኩል ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ አይቻልም – ዶ/ር ይልቃል ከፋለ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የፍትህ ስርዓቱን ማረጋገጥ ካልተቻለ ዘላቂ ሰላምም ሆነ እኩል ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ አይቻልም ሲሉ የአማራ ክልል ርዕስ መስተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለ ገለጹ።

የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት (ዩ ኤስ ኤይድ) ፍትህ ተግባራት ከኢትዮጵያ ጋር በመተባበር የፍርድ ቤቶች ማቋቋሚያና የዳኞች አስተዳደር ጉባዔ ረቂቅ አዋጆችን በተመለከተ ከባለድርሻ አካላት ጋር የምክክር መድረክ እያካሄደ ነው ።

መድረኩን በይፋ ያስጀመሩት የአማራ ክልል ርዕስ መስተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለ የፍትህ ስርዓቱን ማረጋገጥ ካልተቻለ ዘላቂ ሰላምም ሆነ እኩል ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ አይቻልም ሲሉ ገልጸዋል::

ደንብና ስርዓት ብቻውን ለውጥ አያመጣምና ብቃት ያለው፣ ከራሱ በላይ ለህዝብ የሚያስብ፣ ለህልናው የሚያድር ዳኛ እንዲኖር መስራት ያስፈልጋልም ነው ያሉት።

የፍትህ ተግባራት በኢትዮጵያ ኃላፊ ደቪድ ዲ ጃይልስ ፥ ረቂቆቹ ጥናት የተደረገባቸውና የፍትህ ስርዓቱን ለማሻሻል በሚያግዝ መልኩ የተዘጋጁ ናቸው ብለዋል።

በሰላም አስመላሽ

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.