Fana: At a Speed of Life!

የፓሊዬ ክትባትን በአምስት ክልሎች እና በሁለት ከተማ አስተዳደሮች መስጠት ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 27፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የፓሊዬ ክትባትን በአምስት ክልሎች እና በሁለት ከተማ አስተዳደሮች መስጠት ተጀመረ።
በዚህም በደቡብ፣ ኦሮሚያ፣ ሶማሌ፣ ሐረሪ ክልሎች እና በአዲስ አበባ እና ድሬዳዋ ከተማ አስተዳደሮች የፓሊዬ ክትባት መስጠት ተጀምሯል።
ከዛሬ ጀምሮ ለተከታታይ አራት በሚቆየው በዚህ የፖሊዬ ክትባት እድሜያቸው ከአምስት ዓመት በታች ለሆኑ 7 ሚሊየን ህፃናት ይሰጣል።
ማህበረሰቡ ይህን አውቆ ልጆቻቸውን ቤት ለቤት ለሚመጡ የጤና ባለሞያዎች እንዲያስከትብ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አሳስባል፡፡
የፖሊዬ ክትባት ዘመቻ የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ደረጀ ዱጉማ እና የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ አስቻው አባይነ አስጀምረዋል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.