Fana: At a Speed of Life!

የፓርላማ አባላት የአየር ኃይል አባላትን እና ሠራተኞችን አወያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥር 10፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነት እና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ቡድን አባላት የኢፌዴሪ አየር ኃይል የሠራዊት አባላትን እና ሲቪል ሠራተኞችን በተቋማዊ የሥራ ክንውን ዙሪያ አወያይተዋል፡፡

ቡድኑ ሰሞኑን በኦሮሚያ ክልል በቢሾፍቱ ከተማ በሚገኙ የሀገር መከላከያ ሚኒስቴር ተቋማት ባካሄደው የመስክ ምልከታ ወቅት ከአየር ኃይል አባላትን እና ሠራተኞች ጋር ተወያይቷል ፡፡

በውይይቱም በአካዳሚክ ዘርፍ ከሚገኙ ሰልጣኝ ተማሪዎች እስከ አብራሪዎች ድረስ በየመድረኮቻቸው የተሳተፉ ሲሆን፤ የተቋሙ ሲቪል ሠራተኞችም በተዘጋጀላቸው መድረክ ተወያይተዋል፡፡

ባካሄደው ውይይትም የመጀመሪያ ደረጃ ግብረ-መልስ የሰጠ ሲሆን፤ በቅርቡ የተደራጀ የጽሑፍ ግብረ-መልስ እንደሚሰጥም ይጠበቃል፡፡

ከዚህም ባሻገር ከሰበሰባቸውን መረጃዎች በመነሳት ከሀገር መከላከያ ሚኒስቴር ጋርም እንደሚወያይ የቡድኑ አስተባባሪ አቶ ጴጥሮስ ወልደሰንበት አመላክተዋል፡፡

የቡድኑ አባላትም የኢፌዴር አየር ኃይልን በሁሉም የሥራ ክፍሎች ተዘዋውረው የተመለከቱ ሲሆን ላነሷቸው ጥያቄዎችም ከተቋሙ ሙያተኞች ምላሾች እንደተሰጣቸው ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.