Fana: At a Speed of Life!

የፓዊ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ጉዳት ለደረሰባቸው የሰራዊት አባላት ድጋፍ ለማድረግ የህክምና ቡድን ሽኝት አደረገ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኮሌጁ በአሸባሪው ህወሃት አማካኝነት በተከፈተው ጦርነት ጉዳት ለደረሰባቸው የሰራዊት አባላት የህክምና ድጋፍ ለመስጠት ፈቃደኛ የሆኑ የሃኪሞች ቡድን ሽኝት አድርጓል።
11 አባላትን ያካተተው የህክምና ቡድን ወደ ባህር ዳር ከተማ በማቅናት በሰሜን ምዕራብ ዕዝ ሪፈራል ሆስፒታል ውስጥ ለአንድ ወር የሚቆይ የበጎ አድራጎት ስራ እንደሚሰራ የፓዊ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ዲን አቶ አጋጀ አለማየሁ ተናግረዋል።
የህክምና ቡድኑ ሙያዊ ድጋፍ ከማድረግ ባለፈ ከ200 ሺህ ብር በላይ ወጪ በማድረግ የአልባሳትና የተለያዩ መድሃኒቶችን ወደ ስፍራው ይዞ ማቅናቱንም ነው ዲኑ የገለጹት፡፡
ኮሌጁ ከአሁን በፊት ለሀገር መከላከያ ሰራዊት የተለያዩ ድጋፎችን ያደረገ መሆኑን ጠቁመው፥ አሁንም በቀጠናው የህግ የበላይነትን እያስከበረ ከሚገኘው ኮማንድ ፖስት ጋር በመነጋገር አስፈላጊውን ስንቅ በማዘጋጀት የህክምና ቡድኑ አካላዊና ስነ ልቦናዊ ድጋፍ ለማድረግ እንደተሸኙ አቶ አጋጀ አብራርተዋል።
የህክምና ቡድኑ አባላት በበኩላቸው በተሰማሩበት የሙያ መስክ ለሀገር ክብር ሲሉ ጉዳት ለደረሰባቸው አካላት አስፈላጊውን ድጋፍ በማድረግ ሀገራዊ ግዴታቸውን ለመወጣት ቁርጠኛ መሆናቸውን ከመተከል ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.