Fana: At a Speed of Life!

የፕሬዚዳንት ትራምፕ የቀድሞ አማካሪ የ40 ወራት እስራት ተፈረደባቸው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 13፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የረጅም ጊዜ አማካሪ የነበሩት ሮጀር ስቶን የ40 ወራት እስራት ተፈረደባቸው።

ሮጀር ስቶን በ2016ቱ የአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ የሩሲያን ጣልቃ ገብነት ለሚመረምረው ምክር ቤት የሀሰት የምስክርነት ቃል ሰጥተዋል በሚል ክስ ቀርቦባቸዋል።

ከዚህ ባለፈም ከፍ ያለ የህግ ጥሰት ፈጽመዋል በሚልም ተወንጅለዋል።

ይህን ተከትሎም በዋሽንግተን ዲሲ የሚገኘው ፍርድ ቤት የሶስት አመት ከ4 ወራት እስር በይኖባቸዋል።

በተጨማሪም 20 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ቅጣት እና 250 ሰዓታት የማህበረሰብ አገልግሎት እንዲሰጡም ወስኖባቸዋል።

ከውሳኔው በኋላ ፕሬዚዳንት ትራምፕ ሮጀር ስቶን ቅጣቱ አይገባቸውም ሲሉ ተደምጠዋል፤ ዳኛ አሚ በርማንንም “ፀረ ትራምፕ አክቲቪስት” ሲሉ ገልጸዋቸዋል።

የሮጀር ጠበቃ በበኩላቸው ደንበኛቸው ፍርዱን የሚቀበሉበት ምክንያት እንደሌለ ገልጸዋል።

ችሎቱን የመሩት ዳኛ አሚ በርማን ደግሞ “ሮጀር ለፕሬዚዳንት ትራምፕ በመቆማቸው ሳይሆን ለፕሬዚዳንቱ ሽፋን በመስጠት ክስ ተመስርቶባቸዋል” ነው ያሉት።

ግለሰቡ በእርሳቸው ላይ ያልተገባ ዛቻና ባህሪ ማሳየታቸውን በመጥቀስም እርሳቸው ሰው እንጅ ሌላ አይደሉምም ብለዋል።

ሮጀር ስቶን ከ1970ዎቹ ጀምረው ከሪፐብሊካኖች ጋር ሲሰሩ የቆዩ ሲሆን፥ ከ1990ዎቹ ጀምሮ ደግሞ የፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የቅርብ ወዳጅና አማካሪ ሆነው አገልግለዋል።

ምንጭ፡-አልጀዚራ እና ቢቢሲ

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.