Fana: At a Speed of Life!

የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ በጅግጅጋ ተጀመረ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 16 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ዕድሜያቸው ከአምስት አመት በታች ለሆኑ ህፃናት የሚሰጠው የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ ዛሬ በጅግጅጋ ተጀምሯል ።
ክትባቱ ከዛሬ ጀምሮ እስከ ታህሳስ 19 ቀን 2013 ዓ.ም በሁሉም የሶማሌ ክልል ዞን፣ ወረዳና የከተማ አስተዳደሮች የሚሰጥ መሆኑ ታውቋል፡፡
አራት ቀናት የሚቆየውን ይህን የክትባት ዘመቻ የሶማሌ ክልል ጤና ቢሮ ምክትል ቢሮ ሐላፊ አቶ መሐመድ መሐሙድ እና የዓለም ጤና ድርጅት ተወካይና የክልል አመራሮች አስጀምረውታል፡፡
የፖሊዮ ምልክት በሶማሌ ክልል ባይታይም ከአጎራባች ሐገራት ማለትም ሶማሊያ፣ ኬንያና ጅቡቲ ጋር በቅርበት ከመዋሰን አንፃር ቀድሞ በዘመቻ መከላከልን ታሳቢ በማድረግ የተጀመረ ነው፡፡
በዚህም ክትባቱን ቤት ለቤት ለሚሰጡ ባለሙያዎች ወላጆች አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርጉ ሐላፊው አቶ መሐመድ መሐሙድ ማሳሰባቸውን የሶማሌ ክልል ቴሌቪዥን ዘግቧል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.