Fana: At a Speed of Life!

የ16ኛው የብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን በዓል ዋዜማ በድሬዳዋ መከበሩን ቀጥሏል

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 28 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ነገ በድሬዳዋ ከተማ በድምቀት የሚከበረው 16ኛውን የብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀንን ምክንያት በማድረግ ዛሬ የዋዜማ በዓሉ በድሬዳዋ ሚሊኒየም አዳራሽ እየተከበረ ይገኛል ።

በዝግጅቱ ላይ የፌደሬሽን ምክርቤት አፈጉባኤ አቶ አገኘሁ ተሻገርን ጨምሮ የተለያዩ የስራ ሀላፊዎች፣ የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች፣ የአፍሪካ ቀንድ አገራት (የጂቡቲ፣ ሶማሊያ፣ ኤርትራ ኬንያ እና ደቡብ ሱዳን አምባሳደሮች ) ተገኝተዋል።

በመድርኩ የተለያዩ አገራዊ እና ለአገር መከላከያ ሰራዊቱ አለኝታነትን የሚያንፀባርቁ ሙዚቃዎች ቀርበዋል።

ነገ በሚከበረው 16ኛው የብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀንም ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴን ጨምሮ፥ የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ደመቀ መኮንን እንዲሁም ሌሎች የክልል ከፍተኛ ባለስልጣናት ይገኛሉ።

መነሻው ህገመንግስቱ የፀደቀበት ቀን ያደረገዉ የብሔር፣ ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ቀን በዓል አላማዉ የኢትዮጵያ የብሔር ብሔረሰቦችን ትስስር ማጠናከር አድርጎ ላለፉት 15 ጊዜያት በተለያዩ ክልሎች ሲከበር ቢቆይም ባለፉት አመታት ወንድማማችነትን ከማጠናከር አንፃር የተከናወኑት ስራዎች ግን ውጤታማ ስራዎች ያልተከወኑበት መሆኑን የፌዴሬሽን ምክርቤት አፈጉባኤ አቶ አገኘሁ ተሻገር ተናግረዋል

የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት አፈጉባኤ ወ/ሮ ፈቲያ አደም በበኩላቸዉ፥ ” ቀደም ሲል የብሔሮች፣ ብሔረሰቦች በዓል ለዘመናት ህብረ ብሔራዊነት ከማስከበር ይልቅ ሲነጣጥለን የቆየው ሀይል እየተደመሰሰ ባለበት በዚህ ወቅት መከበሩ የበዓል አከባበሩን ትርጉም ይሰጠዋል ” ሲሉ ተናግረዋል ።

”ወያኔ ሲገባ ነጣጠለን ሲወጣ ደግሞ አንድ አደረገን” ያሉት የፌዴሬሼን ምክር ቤት አቶ አገኘሁ ተሻገር ÷ የሽብር ቡድኑ ህውሓት አሁንም ህገመንግስቱን እና ህገመንግስታዊ ስርዓቱን ለመናድ የቀጥታ ጦርነት ፣ የፖለቲካ ፣ ኢኮኖሚ እና ዲፕሎማሲያዊ እና የሚዲያ ጦርነትን በይፋ ከፍቶብን ቆይቷል ብለዋል ።

ቀጣዮቹ ጊዜያት አንዱ የሌላውን እሴት በመጋራት አብሮ የሚኖርበት ሊሆን እንደሚገባም አንስተዋል ።

በፀጋዬ ወንድወሰን

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.