Fana: At a Speed of Life!

የ17 ዓመት በታች የምስራቅና መካከለኛ አፍሪካ ዋንጫ ኘሮግራም ላይ ማስተካከያ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 3፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የ17 ዓመት በታች የምስራቅና መካከለኛ አፍሪካ ዋንጫ ዛሬ የመክፈቻ ጨዋታ በሩዋንዳና በታንዛኒያ መካከል እንዲደረግ ፕሮግራም ወጥቶለት ነበር።
ነገር ግን በኮቪድ ምክንያት ወደ ሰኞ የተቀየረ ሲሆን የመክፈቻው ጨዋታ በነገው እለት በኢትዮጵያና በኬንያ መካከል ከቀኑ 9:00 ሰዓት እንደሚደረግ ማምሻውን በተካሄደው የቅደም ጨዋታ ስብሰባ ተገልጿል።
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን እንዳስታወቀው የኮቪድ 19 ምርመራ ካፍ ባስቀመጠው መመሪያ መሰረት በየ48 ሰዓታት ይደረጋል።
በዚህ የቅድመ ጨዋታ ስብሰባ ላይ የውድድሩ የቴክኒክ አባል የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልና የቴክኒክና ልማት ኮሚቴ ሰብሳቢ ኢንስትራክተር ሰውነት ቢሻዉ ተገኝተዋል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.