Fana: At a Speed of Life!

የ2013 ቶታል ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ውድድር ዝግጅት ተጠናቋል

አዲስ አበባ ፣ታህሳስ 30 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በመጪው እሁድ ለሚካሄደው የ2013 ቶታል ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ውድድር የዝግጅት ሥራ መጠናቀቁ ተገለጸ።
የኮቪድ-19 ቅድመ ጥንቃቄዎችን ታሳቢ በማድረግ ጥር 2 ቀን 2013 ዓ.ም የሚካሄደው 20ኛው ቶታል ታላቁ ሩጫ 12 ሺህ 500 ተሳታፊዎች ብቻ እንደሚኖሩት ታውቋል።
ውድድሩ መነሻውን መስቀል አደባባይ፤ መድረሻው ደግሞ አትላስ አካባቢ እንደሚሆን የገለጸው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት የዝግጅት ሥራው መጠናቀቁንም ተገልጿል።
የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር የስፖርት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሀብታሙ ሲሳይ እንዳሉት “ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ለአገር ገጽታ ግንባታ ብሎም ለቱሪዝም መስፋፋት ትልቅ ሚና ያለው ከመሆኑ ባሻገር የኢትዮጵያዊያን አንድነት፣ ፍቅርና ሰላም መገለጫ ሆኗል” ።
የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ መስራች እና የቦርድ ሊቀመንበር ሻለቃ አትሌት ኃይሌ ገብረስላሴ በበኩላቸው፤ “ታላቁ ሩጫ በዓለም ላይ አንጋፋ ከሚባሉ የጎዳና ውድድሮች አንዱ ሲሆን ዘንድሮ 20ኛ ዓመቱ ላይ ደርሷል” ብለዋል።
በእስካሁኑ የ20 ዓመት የውድድር ጉዞው የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ላደረጉ አካላትም ምስጋና አቅርበዋል።
በዘንድሮ ውድድር ከጤና ሯጮች በተጨማሪ 300 የሚሆኑ ወንድ እና ሴት አትሌቶች የሚወዳደሩ ሲሆን አሸናፊ ለሚሆነው አትሌትም የ100 ሺህ ብር ሽልማት እንደሚሰጥ ተገልጿል።
በተጨማሪም የጃፓን፣ ፊንላንድ፣ ፖላንድ እና ቱርክ አምባሳደሮችና ዲፕሎማቶችም የውድድሩ ተሳታፊዎች እንደሚሆኑ ኢዜአ ዘግቧል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.