Fana: At a Speed of Life!

የ50 ዓመት የወርቅ ኢዩቤልዩ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና በአዲስ አበባ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 28፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የ50 ዓመት የወርቅ ኢዩቤልዩ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና በአዲስ አበባ ስታዲየም በተለያዩ የማጣሪያ ውድድሮች ዛሬ ተጀምሯል።
ሻምፒዮናው በተሳታፊ ቡድኖች የሰልፍ ትርኢት በመከላከያና በፌደራል ፖሊስ ማርች ባንድ በታጅበ ስነስርዓት ነው በአዲስ አበባ ስታዲየም የተጀመረው።
ይህም ሻምፒዮና ከዛሬ ጀምሮ እስከ ሚያዚያ 3 ቀን 2013 ዓ.ም በተለያዩ ውድድሮች ይካሄዳል።
በመክፈቻ ስነ ስርዓቱም ላይ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ ባስተላለፈችው መልዕክት እንኳን ለ50ኛ ዓመትየኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና አደረሳችሁ ብላለች።
አትሌቲክስ ኢትዮጵያን በዓለም አቀፍ አደባባይ ያስተዋወቀ ነው÷ በመሆኑም ፌዴሬሽኑ ስፖርቱን ለማስፋፋት እና ለማሳደግ እየሰራ ነው ሲሉ ገልጸዋል።
አያይዘውም ሻምፒዮናው በ50 ዓመት የውድድሩ ታሪኩም በኦሊምፒክና በዓለም ሻምፒዮና ሀገርን የሚወክሉ አትሌቶች ያፈራ ነው ብለዋል።
በዚህም ውድድር በኦሊምፒክና በዓለም ሻምፒዮና ሀገርን የሚወክሉ አትሌቶች የሚወጡበት መድረክ እንደሚሆን ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።
የ50 ዓመት የወርቅ ኢዩቤልዩ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮናውን በይፋ የከፈቱት የኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ኤልያስ ሽኩር በበኩላቸው÷ ኢትዮጵያ ለምትታወቅበት ለአትሌቲክስ ስፖርት ማደግ እንዲሁም ለቶኪዮ ኦሊምፒክ ዝግጅት ኮሚሽኑ ከፌዴሬሽኑ ጎን መሆኑን ተናግረዋል።
ሻምፒዮናው ኢትዮጵያን በዓለም አቀፍ አደባባይ የሚያስጠሩ አትሌቶች የሚፈሩበት እንደሚሆንም ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።
አያይዘውም ከዚህ ቀደም የምንታወቅባቸውን የውድድር አይነቶች በመጠበቅ ታዳጊዎች እና ውድድር ዓይነቶች ለማስፋፋት መስራት ይገባናልም ብለዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-

https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.