Fana: At a Speed of Life!

የ6ኛውን ሀገራዊ ምርጫ የመገናኛ ብዙኃን አጠቃቀምና ድልድል ዕጣ ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 30 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የ6ኛውን ሀገራዊ ምርጫ የመገናኛ ብዙኃን አጠቃቀምና ድልድል ዕጣ ይፋ ሆኗል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ ውብሸት አየለ እና የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር መሐመድ ኢድሪስ መሐመድ በተገኙበት ትናንት የመገናኛ ብዙኃን አጠቃቀምና ድልድል ዕጣ ማውጣት ተከናውኗል።

የሁሉም ፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች ተሳታፊ የሆኑበት የዕጣ ማውጣት ሂደት 57 መገናኛ ብዙኃን ተቋማት የተካተቱበት ሲሆን፤ ከእነዚህም ውስጥ ሰባት ጋዜጦች፣ 21 የሬዲዮ ጣቢያዎች እንዲሁም 29 የቴሌቪዥን ጣቢያዎች ይገኙበታል።

የብሮድካስት ባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ ባበለጸገው ቴክኖሎጂ የተከናወነው የዕጣ ማውጣት 46 ፖለቲካ ፓርቲዎችን ያካተተ ነው።

አጠቃቀምና ድልድሉ ከዛሬ ጀምሮ እስከ ግንቦት 23 ቀን 2013 ዓ.ም. ተፈጻሚ ይሆናል።

በአፈጻጸም ሂደቱ ላይ ለሚያጋጥሙ እክሎች ፖለቲካ ፓርቲዎቹ ከቦርዱ ጋር በመምክር መፍትሄ የሚያገኙ ሲሆን፤ የመገናኛ ብዙኃን ተቋማቱም እንደዚሁ ከብሮድካስት ባለሥልጣኑ ጋር እየመከሩ በጋራ መፍትሔ የሚሰጥበት መሆኑን ከቦርዱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.