Fana: At a Speed of Life!

የ8ኛና 12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የሶስት ሰሚስተሮችን ትምህርት ብቻ ይሸፍናል

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 16፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የ2012 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል  ክልላዊ እና  የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሄራዊ  ፈተና ሶስት ሲሚስተሮችን ብቻ ያካተተ መሆኑን የትምህርት ሚኒስትር ሚኒስትር ዶክተር ጌታሁን መኩሪያ ተናገሩ።

በዚህም መሰረት የ11ኛ ክፍል ሁለቱም ሲሚስተሮች እና የ12 ኛ ክፍል የመጀመሪያው ሲሚስቴር በፈተና አወጣጥ ሄደት ውስጥ የሚካተት ይሆናል።

በተመሳሳይ የ7ኛ ክፍል ሁለቱም ሲሚስተሮች እና የ8ኛ ክፍል የመጀመሪያው ሲሚስቴር ብቻ በ8ኛ ክፍል ፈተና ውስጥ የሚካተት መሆኑም ተገልጿል።

ትምህርት ቤቶችም  ያለፉትን ሶስት ሲሚስተሮች ዋና ዋና ነጥቦች ላይ  የማካካሻ ትምህርት ለ45 ቀን እንደሚሰጡ ተነግሯል።

ክልላዊ እና ሀገር አቀፍ ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎችም ትምህርታቸውን በትኩረት እንዲከታተሉ እና አስፈላጊውን ዝግጅት እንዲያደርጉ ሚኒስትሩ ጥሪ አቅርበዋል።

በዛሬው እለትም በአዲስ አበባ የሚገኙ  የ8ኛ እና 12ኛ ክፍል ተማሪዎች ትምህርት ጀምረዋል፡፡

ያለፈው ዓመት የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና በኦንላይን የሚሰጥ መሆኑንም ከትምህርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.