Fana: At a Speed of Life!

የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና እስከ ታህሳስ 30 ቀን ይጠናቀቃል- ትምህርት ሚኒስቴር

አዲስ አበባ፣ ህዳር 25፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የትምህርት ሚኒስቴር ባስቀመጠው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና በሁሉም ክልሎች እስከ ታህሳስ 30 ቀን እንደሚጠናቀቅ ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።

ይህን ተከትሎም የክልል ትምህርት ቢሮዎች ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመወያየትና አስፈላጊውን ዝግጅት በማድረግ ፈተናውን በተያዘለት የጊዜ ገደብ ለመስጠት የራሳቸውን የጊዜ ሰሌዳ በማውጣት ወደ ስራ የገቡ እና በቀጣይ የሚገቡ እንዳሉ ተጠቁሟል።

በዚህም መሰረት የሀረሪ ክልል ከታህሳስ 7 እስከ 9 እንዲሁም የአማራ ክልል ከታህሳስ 12 እስከ 14 ቀን ድረስ ፈተናውን ለመስጠት መዘጋጀታቸውን አስታውቀዋል።

ሌሎች ክልሎችም በቀጣይ ቀናት ፈተናው የሚሰጥበትን ቀን ይፋ እንደሚያደርጉ ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

በአዲስ አበባ ከተማ የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ከትናንት ጀምሮ መሰጠት መጀመሩ ይታወሳል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.