Fana: At a Speed of Life!

ዩኒቨርሲቲ መግባቴን ለጊዜው ገታ አድርጌ ለሀገሬ መዝመትን መርጫለሁ-ወ/ር ሜቲ አዱኛ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) “ሀገር ያለወታደር ባዶ በመሆኗ ዩኒቨርሲቲ መግባቴን ለጊዜው ገታ አድርጌ ቅድሚያ ለሀገሬ መዝመትን መርጫለሁ” ትላለች ተመራቂዋ ወታደር ሜቲ አዱኛ፡፡
 
የጦላይ ከፍተኛ ባለሌላ ማዕረግተኛ ማስልጠኛ ትምህርት ቤት በመሠረታዊ ውትድርና በ2ኛ ዙር ያሰለጠናቸውን የሰራዊት አባላት አስመርቋል።
 
ከተመራቂዎች መካከል በ12ኛ ክፍል የአገር አቀፍ ፈተና ከፍተኛ ውጤት አስመዝግባ “ቅድሚያ ለአገሬ ህልውና” በማለት ወታደራዊ ማሰልጠኛ የገባችው ተማሪ ትገኝበታለች።
 
በዩኒቨርሲቲ መግቢያ ከፍተኛ ውጤት በማምጣት ምደባው ጅማ ዩኒቨርሲቲ የደረሳት ወጣት “አገር ያለወታደር ባዶ በመሆኗ ቅድሚያ ለአገሬ መዝመትን መርጫለሁ” ብላለች።
 
በስልጠና ቆይታው ወታደራዊ ሳይንስንና የተግባር ልምምዶችን በበቂ ሁኔታ መቅሰሟን ገልፃ፤ ኢትዮጵያን አፈርሳለሁ ብሎ የተነሳውን ሃይል ለመደምሰስ ዝግጁ ነኝ ትላለች።
 
ከማዕከሉ በቂ ስልጠና በማግኘቴ በየትኛውም ቦታና ሁኔታ አገሬን ለማገልገል ተዘጋጅቻለሁ ብላለች ወታደር ሜቲ አዱኛ።
 
ኢትዮጵያን ከውጭና ከአገር ውስጥ ወራሪዎች ለመከላከል በሙሉ አቅሟ ለመስራት ዝግጁ መሆኗን አረጋግጣ ወጣቶች የአገር መከላከያ ሰራዊትን እንዲቀላቀሉ ጥሪ አቅርባለች።
 
በኢንጅነሪንግ ዘርፍ ሰራዊቱን የተቀላቀለው መሰረታዊ ወታደር እስራኤል ካሳሁን÷ በ12ኛ ክፍል ከፍተኛ ውጤት በማምጣት በዘርፉ ሰራዊቱን በራሱ ፍቃድ መቀላሉን ለኢዜአ ተናግሯል።
 
ኢትዮጵያን አፈርሳለሁ ብሎ የተነሳውን አሸባሪ ለማጥፋት በእልህ መዘጋጀቱንም ነው የገለጸው።
 
በማሰልጠኛ ማእከሉ ያገኘናቸው ወንድማማቾቹ ወታደሮች ኪያ ተገኝ እና ካሳሁን ተገኝ በጀግንነት ለሀገራቸው መቆማቸውን ተናግረዋል።
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.