Fana: At a Speed of Life!

ዩኔስኮ ዓለም አቀፋዊ ችግሮችን ለመፍታት የሚያደርገው ጥረት ልዩ መለያው ነው- ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ

አዲስ አበባ፣ ጥር 23፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በመንግስታቱ ድርጅት የትምህርት፣ የሳይንስ እና የባህል ማዕከል (ዩኔስኮ)ዓለም አቀፋዊ ችግሮችን ለመፍታት የሚያደርገው ጥረት ልዩ መለያው መሆኑን የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ ገለፁ።

የትምህርትን በጎ አስተዋጽዎ እንደገና መቅረጽና ማስፋት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ምክረ ሀሳብ የሚያቀርበው ዓለም ዓቀፍ ኮሚሽን በፈረንሳይ ፓሪስ ስብሰባውን ባደረገበት ወቅት ነው ፕሬዚዳንቷ ይህንን የገለፁት።

በፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ የሚመራው ኮሚሽኑ፤ የመጀመሪያ ስብሰባውን በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የትምህርት፤የሳይንስና የባህል ማዕከል ዋና ጽህፈት ቤት አካሂዷል።

ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ በስብሰባው ላይ፥ ዩኔስኮ ከመላው ዓለም የሚመለከታቸውን ሁሉ በማሰባሰብ አለም አቀፋዊ ችግሮችን ለመፍታት የሚያደርገው ጥረት ልዩ መለያው ነው ብለዋል።

ከኮሚሽኑ ብዙ የሚጠበቁ ውጤቶች እንዳሉ ያስታወሱት ፕሬዝደንት ሣህለወርቅ፥ በመጪው ጊዜያት የሚያጋጥሙ ችግሮችን ለመፍታት ካለንበት ዘመን በላይ አሻግረን ማሰብ ይኖርብናል ሲሉም ተናግረዋል።

እየተወሳሰበ በመጣው አለም አቀፍ መስተጋብር ውስጥ የትምህርትን በጎ አስተዋጽዎ እንደገና መቅረጽና ማስፋት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ምክረ ሀሳብ የሚያቀርበው ዓለም ዓቀፍ ኮሚሽን ባለፈው መስከረም በኒዮርክ ይፋ መደረጉ እንደሚታወስ የፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት መረጃ ያመለክታል።

የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ በፈረንሳይ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው ባገለገሉበት እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር ከ2002- 2006 ድረስ በመንግስተቱ ድርጅት የትምህርት፤ የሳይንስና የባህል ድርጅት የኢትዮጵያ ተወካይ ሆነውም ሰርተዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.