Fana: At a Speed of Life!

ዩዌሪ ሙሴቪኒ መንግስት በሰሜን ኢትዮጵያ የተፈጠረውን ግጭት በሰላም ለመፍታት የወሰደውን እርምጃ እንደሚያደንቁ ገለፁ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 29፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኡጋንዳውፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቪኒ መንግስት በሰሜን ኢትዮጵያ የተፈጠረውን ግጭት በሰላም ለመፍታት የወሰደውን እርምጃ እንደሚያደንቁ ገለፁ።

አምባሳደር አለምፀሀይ መሰረት  ወቅታዊ ጉዳዮችን በተመለከተ ከኡጋንዳው ፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቪኔ ጋር ተወያይዋል፡፡

በውይይታው አምባሳደር አለምፀሀይ መንግስት በሰሜን ኢትዮጵያ የተፈጠረውን ጦርነት በሰላም ለመፍታት እየወሰደ ያለውን ቁርጠኛ እርምጃዎች ለፕሬዚዳንቱ ገለፃ አድርገውላቸዋል፡፡

የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ እንዲሁም በቀጠናው የአየር ንብረት ለውጥ ጫናን አስቀድሞ ለመቋቋም በተከታታይ አመታት ስለተካሄደው የአረንጓዴ አሻራ ስራዎች አብራርተዋል፡፡

የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል ኡጋንዳ ባዘጋጀችው ቀጠናዊ የሚኒስትሮች የአየር ንብረት ኮንፈረንስ የምስራቅ አፍሪካ መንግስታት የጋራ አቋም እንዲያራምዱ ኡጋንዳ የወሰደችውን ተነሳሽነት አድንቀዋል፡፡

የኡጋንዳ ፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቪኒ በበኩላቸው መንግስት በሰሜን ኢትዮጵያ የተፈጠረውን ግጭት በሰላም ለመፍታት የወሰደውን እርምጃ እንደሚያደንቁና የሰላም ንግግር ለማድረግ የተያዘው ዕቅድ እንዳስደሰታቸው ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያ ሰላም መሆን ለቀጠናው ደህንነት ጉልህ ሚና እንደሚጫወት የገለፁት ፕሬዚዳንቱ  ኡጋንዳ እና ኢትዮጵያ ሽብርተኝነትን በጋራ ለመከላከል እና በቀጠናው ሰላምና ጸጥታ ዘርፍ ያላቸውን ትብብር አጠናከሮ መቀጠል እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል፡፡

በውይይቱ ኢትዮጵያ በንግድና ኢንቨስትመንት፣ በቀጠናዊ ሰላም እና ፀጥታ ጉዳዮች እንዲሁም በአየር ንብረት ለውጥ እና በናይል ተፋሰስ ላይ ያላቸውን ትብብር የበለጠ ለማጠናከር በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይም ውይይት መደረጉን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.