Fana: At a Speed of Life!

ዩ ኤስ ኤይድ በአፍሪካ ቀንድ አስቸኳይ የሰብዓዊ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች 105 ሚሊየን ዶላር የሚጠጋ ድጋፍ እየሰጠሁ ነው አለ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሜሪካ የልማት ተራድኦ ድርጅት (ዩ ኤስ ኤይድ) ኢትዮጵያን ጨምሮ በአፍሪካ ቀንድ ለሚገኙና አሳሳቢ የሰብዓዊ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች የሚውል 105 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር የሚጠጋ ድጋፍ እያደረገ መሆኑን ገለጸ።

ተቋሙ በማህበራዊ ትስስር ገጹ ባሰፈረው ጽሑፍ፥ እየተደረገ ያለው አስቸኳይ የምግብ ዕርዳታ በኢትዮጵያ፣ ኬንያና ሶማሊያ ለሚገኙና በተከታታይ በተከሰተው የድርቅ አደጋ ምክንያት የከፋ ጉዳት ለደረሰባቸው ወግኖች ነው ብሏል።

ድጋፉ የዩ ኤስ ኤይድ አጋሮች በቀጠናው ችግር ውስጥ ለሚገኙ ዜጎች አስቸኳይ የሰብዓዊ እርዳታ ፣ የተመጣጠነ ምግብ፣ ንፁህ ውሃ እና መሰል ድጋፎችን በአስፈላጊው ሰዓት እንዲያሰራጩ የሚያስችል መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.