Fana: At a Speed of Life!

ያሬድ ባየህ ብሔራዊ ቡድኑ ከቡርኪና ፋሶ ጋር በሚያደርገው ጨዋታ ይሰለፋል

አዲስ አበባ፣ ጥር 3፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተከላካይ ያሬድ ባየህ ከአንድ ጨዋታ ቅጣት በኋላ ለብሔራዊ ቡድኑ እንደሚሰለፍ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ገለፀ፡፡

የብሔራዊ ቡድኑ ተከላካይ ያሬድ ባየህ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከኬፕ ቬርዴ ጋር ባደረገው ጨዋታ 12 ኛው ደቂቃ ላይ በቀይ ካርድ ከሜዳ መውጣቱ ይታወሳል።

በዚህም አንድ ጨዋታ የሚቀጣ ሲሆን÷ በቀጣይ ሐሙስ ኢትዮጵያ ከካሜሩን የምታደርገው ጨዋታ ብቻ የማይሰለፍ ይሆናል።

ብሔራዊ ቡድኑ ከቡርኪና ፋሶ ጋር በሚያደርገው ጨዋታ ግን ተጫዋቹ እንደሚሰለፍ ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.