Fana: At a Speed of Life!

ያጋጠሙ ችግሮችን በድል ለመወጣት የመገናኛ ብዙሃን ሚና ከፍተኛ ነው – አብርሃም አለኸኝ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 30፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) ያጋጠሙ ችግሮችን በድል ለመወጣት የመገናኛ ብዙሃን ሚና ከፍተኛ ነው ሲሉ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት የስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ አቶ አብርሃም አለኸኝ ተናገሩ፡፡

ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በደሴ ከተማ ያሰገነባውን አዲስ የሚዲያ ኮምፕሌክስ ህንጻ ዛሬ አስመርቋል፡፡

በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ ንግግር ደረጉት አቶ አብርሃም አለኸኝ፥ በደህረ ለውጥ ዜጎችን ያጎሳቆሉ በርካታ ሀገራዊ ተግዳሮቶች መከሰታቸውን አንስተዋል፡፡

ይሁን እንጅ በህብረ ብሄራዊ ወንድማማችንት እና አህትማማችነት መንፈስ እና በህዝቡ መራር ትግል ያጋጠሙ ፈተናዎችን አልፈን ዛሬ ላይ ቆመናል ብለዋል፡፡

በመሆኑም ያጋጠሙ ችግሮችን በድል ለመወጣት የሚያስችሉ መረጃዎችን ተደራሽ ከማድረግ አንፃር የመገናኛ ብዙሃን ሚና ከፍተኛ መሆኑን አመላክተዋል፡፡

መገናኛ ብዙሃን የሀገራችንን የስኬት ታሪኮች ተንትኖ በማቅረብ ሀገራችን የአፍሪካ የብልፅግና ተምሳሌት ልትሆን እንደምትችል በርካታ ማስረጃዎችን በማጣቀስ ማሳየት እንደሚጠበቅባቸውም ገልጸዋል፡፡

በዚህ ረገድ ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ወደ ህዝብ ወርዶ እና ቀርቦ ለመስራት የሚያከናውናቸውን ተግበራት አጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ነው ያስታወቁት፡፡

ለዚህም የተቋሙ የቦርድ አባላት፣ አመራሮች እና የተቋሙ ሰራተኞች ከምንጊዜውም በላይ በትጋት የሚሰሩ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.