Fana: At a Speed of Life!

ደረቅ ቆሻሻን መልሶ በመጠቀም ከ432 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ ተገኘ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 6፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ደረቅ ቆሻሻን መልሶ በመጠቀም ከ432 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ መገኘቱን በአዲስ አበባ ከተማ ደረቅ ቆሻሻ አስተዳደር ኤጀንሲ አስታውቋል።

በአዲስ አበባ የደረቅ ቆሻሻ መልሶ መጠቀምና ዑደት የተሰሩ ስራዎችን የሚያሳይ አውደ ርዕይ በሚኒሊክ አደባባይ በይፋ ተከፍቷል ።

በአዲስ አበባ ከተማ ደረቅ ቆሻሻ አስተዳደር ኤጀንሲ አዘጋጅነት የደረቅ ቆሻሻ መልሶ መጠቀምና ዑደት የተሰሩ ስራዎችን የሚያሳይ አውደ ርዕይ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የመንግሥት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አስተባባሪ አቶ ጃንጥራር አባይ እና በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የማዘጋጃ ቤታዊ ዘርፍ ስራ አስኪያጅ አቶ ጥራቱ በየነ በተገኙበት ተከፍቷል ።

ባለፉት ዘጠኝ ወራትም በደረቅ ቆሻሻ መልሶ መጠቀምና ዑደት ለ3 ሺህ 88 ሴቶች እና ወጣቶች በኮምፖስት፣ በወረቀት እና ካርቶን እንዲሁም በፕላስቲክ ጠርሙስ መልሶ መጠቀም የስራ እድል በመፍጠር 36 ሺህ 280 ቶን ምርት ተሰብስቧል ።

በዚህም ከሚሰበሰበው ደረቅ ቆሻሻ በአግባቡ በመያዝ እና በመልሶ በመጠቀም በሀገር ውስጥ እና ወደ ውጭ በመላክ ከ432 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ በመሰብሰብ በዘርፉ የተሰማሩ ዜጎችን ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን በአውደ ርዕዩ መክፈቻ ላይ ተገልጿል ።

በተያያዘም “አካባቢየን በማፅዳት ለከተማየ ፅዳት አምባሳደር ነኝ” በሚል መሪ ቃል ባለፉት ሁለት ወራት ሲካሄድ የነበረው ከተማ አቀፍ የጽዳት ዘመቻ ንቅናቄ የእውቅና ማጠቃለያ መርሐግብር በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በመካሄድ ላይ እንደሚገኝ ከአዲስ አበባ ከተማ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.