Fana: At a Speed of Life!

ደራሲ እና ተዋናይ ተባባሪ ፕሮፌሰር ተስፋዬ ገሰሰ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 7፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ደራሲ እና ተዋናይ ተባባሪ ፕሮፌሰር ተስፋዬ ገሰሰ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።

ተባባሪ ፕሮፌሰር ተስፋዬ የተለያዩ መፅሃፍትን የደረሱ ሲሆን በተለያዩ ፊልሞች እና ድራማዎች ላይም በተዋናይነት ተሳትፈዋል።

ብሄራዊ ቴዓትር ቤት የሽኝት ፕሮግራም እንደሚያዘጋጅ የተገለፀ ሲሆን ቀብራቸው በቅድስት ስላሴ ካቴድራል ቤተክርስቲያን እንደሚፈፀም ተጠቁሟል።

በርካታ ተውኔቶች ላይ የትወና ችሎታቸውን ያስመሰከሩት ተባባሪ ፕሮፌሰር አጫጭር ልቦለዶችና ግጥሞቻቸው በሩሲያኛ ተተርጉመው ሩሲያ ውስጥ ታትመዋል፡፡

ተባባሪ ፕሮፌሰር ተስፋዬ መተከዣ (ግጥምና ቅኔ) ፣ ጥላሁን ግዛው፣ ዕቃው፣ የሺ ፣ አባትና ልጆች፣ ላቀችና ደስታ፣ ተሐድሶ የተሰኙ ተውኔቶችን ደርሰዋል።

እንዲሁም የዑመር ኻያምን ልቦለዳዊ የሕይወት ታሪኩና ሩብ አያቶቹ የትርጉም መፅሃፍ ለአንባቢያን አድርሰዋል።

ተባባሪ ፕሮፌሰር ተስፋዬ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቴዓትር እና ጥበባት ኮሌጅ ለበርካታ ዓመታት በመምህርነት አገልግለዋል።

በሐረርጌ  በ1929 ዓ.ም የተወለዱት ተባባሪ ፕሮፌሰር ተስፋዬ በ84 አመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.