Fana: At a Speed of Life!

ዲያስፖራው በዱከም እና ገላን የኢንዱስትሪ መንደሮች በኢንቨስትመንትዘርፍ እንዲሰማራ ጥሪ ቀረበ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢንዱስትሪ መንደርነታቸው በሚታወቁት ዱከም እና ገላን ከተሞች ዲያስፖራው በኢንቨስትመንት ዘርፍ እንዲሰማራ የከተማዎቹ አስተዳደሮች ጥሪ አቀረቡ።

በከተሞቹ ከዚህ ቀደም በርካታ የሀገር ውስጥ እና የወጭ ባለሀብቶች በተለየያዩ የኢቨስትመንት መስከሎች ተሰማርተዋል ያሉት የየከተሞቹ አስተዳደር የስራ ሀላፊዎች ፣ አሁን ላይ መንግስት ያቀረበውን ጥሪ ተቀብለው ወደ ሀገር ቤት የገቡ የዲያስፖራው ማህበረሰብ አባላት ወደ ከተሞቹ በመምጣት እንዲያለሙ ዝግጅት ማድረጋቸውን ተናግረዋል።

የዱከም ከተማ ከንቲባ አቶ አብዱልጀሊል አብዱሮ፥ ከተማዋ የኢንዱስትሪ መንደር በመሆኗ በብዙ አልሚ ባለሀብቶች ትመረጣለች ብለዋል።

አሁንም ማልማት ለሚችሉ ዳያስፖራዎች አገልግሎት አሰጣጥን ቀልጣፋ በማድረገና ለኢንቨስትመንት የሚሆን ቦታ በማዘጋጀት በመጠባበቅ ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል።

እስካሁንም ከተማዋ ያላትን የኢንቨስትመንት አማራጮች ለመመልከት ወደ ከተማዋ እየመጡ ያሉ ባለሀብቶች መኖራቸውንም ገልጸዋል።
በተመሳሳይ የገላን ከተማ ከንቲባ ወ/ሮ ወይንሸት ግዛው እንደተናገሩት፥ በከተማዋ ለበርካታ ዜጎች የስራ እድል የፈጠሩ እና ለራሳቸውም ተጠቃሚ የሆኑ ባለሀብቶች በኢንቨስትመንት ተሰማርተው እንደሚገኙ አስታውሰው፥ ወደ አገር ቤት የገቡ የዳያስፖራ አባላት በከተማዋ በአልሚነት እንዲሰማሩ ጥሪ አቅርበዋል።

በማኑፋክቸሪንግም ሆነ በሌሎች ዘርፎች መሰማራት ለሚፈልጉ ዳያስፖራዎች የከተማው አስተዳደር ሁኔታዎችን እንደሚያመቻች ከንቲባዋ አሳውቀዋል።

ሁለቱም ከተሞች ከአዲስ አበባ በቅርብ ርቀት ላይ በመገኘታቸውና ለኢንቨስትመንት ባላቸው ምቹ ሁኔታ በባለሀብቶች ተመራጭ እንደሆኑም ተገልጿል።

በአዳነች አበበ

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.