Fana: At a Speed of Life!

ዲያስፖራ ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገር ቤት ሲመጡ የደረሰ የአርሶ አደር ሰብል የሚሰበስቡበት እድል ተመቻችቷል

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 14 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) መንግስት ያቀረበላቸውን ሀገራዊ ጥሪ ተቀብለው ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡ ከ1 ሚሊየን በላይ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ወገኖችን በልዩ ሁኔታ ለመቀበል ዝግጅት መደረጉን በአዲስ አበባ የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ መላኬ ዓለማየሁ ገለፁ፡፡

ዋና ስራ አስፈፃሚዋ እነዚህ እንግዶች ወደ ሀገራቸው ሲመጡ ምንም ችግር እንዳያጋጥማቸው ብሎም ደስተኛ ሆነው እንዲስተናገዱ የክፍለ ከተማው አሥተዳደርና ሴክተር መሥሪያ ቤቶች በቅንጅት ሆነው በሠላምና ጸጥታ፣ በአካባቢ ውበት ጥበቃ ስራዎች እንዲሁም በሀገር ባሕልና ቅርስ ላይ እየሰሩ መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡

እንግዶች የሚያርፉባቸው ሆቴሎችና ሊጠቀሙባቸው የሚችሉ ሱፐር ማርኬቶች በቂና ደረጃቸውን የጠበቁ እንዲሆኑ ለማድረግም ከባለሐብቶችና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እየሠሩ መሆናቸውን ዋና ስራ አስፈጻሚዋ ገልጸዋል፡፡

ከ2 ሺህ በላይ እንግዶችን ማስተናገድ የሚችሉ ከ60 በላይ ሆቴሎች መዘጋጀታቸውንም ተጠቁሟል፡፡

በክፍለ ከተማው አርሶ አደሮች ሰብል እንደሚያመርቱ ያነሱት ዋና ስራ አስፈፃሚው፥ ይህ የክፍለ ከተማው ሁኔታ የጎብኚዎችን ዕይታ ይስባል ተብሎ እንደሚጠበቅ መጠቆማቸውን የክፍለ ከተማው ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ ያመለክታል።

ኢትዮጵያውያኑ እና ትውልደ ኢትዮጵያውያኑ የአርሶ አደሮችን ሰብል በመሰብሰብ ወገናዊ አጋርነታቸውን እንዲያሳዩ ሁኔታዎች እንደተመቻቹም ነው የተገለጸው፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.