Fana: At a Speed of Life!

ዳንሻን፣ ባከርን እና ከሽራሮ እስከ ሽሬ ያሉ አካባቢዎችን መከላከያ ሠራዊት ሙሉ በሙሉ መቆጣጠሩ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 29፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የመከላከያ ሠራዊት ዳንሻን፣ ባከርን እና ከሽራሮ አስከ ሽሬ ያሉ አካባቢዎች ሙሉ በሙሉ መቆጣጠሩን የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ምክትል ኤታማዦር ሹም እና የኦፕሬሽን ዘርፍ ኃላፊ ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ አስታወቁ።

ጄኔራል ብርሃኑ ለኢትዮጵያ ነቀርሳ የሆነው ከሀዲው የህውኃት ቡድን ካልተደመሰሰ ሀገር ሰላም እንደማትሆንም ገልጸዋል።

ጄኔራሉ የመከላከያ ሠራዊቱ ዳንሻን፣ ባከርን እና ከሽራሮ አስከ ሽሬ ያሉ አካባቢዎች ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥሮ ወደ ፊት እየገሠገሠ ይገኛል ብለዋል።

መከላከያ በከሀዲ ቡድኑ እጅ ያሉ ከባድ መሳሪያዎች ሙሉ በሙሉ ማውደሙን አመልክተው፣ እንደ ተምች በየቦታው ሠራዊቱን የከበበውን ኃይል እያራገፈ መሆኑን ጠቁመዋል።

“ትናንሽ ክፍሎችን ከቦ የነበረው ኃይልም በሠራዊታችን ታላቅ ጀግንነት ተደምስሰዋል” ብለዋል።

ከፍ ያለ ቁጥር ያለው የክልሉ ልዩ ኃይልና ሚሊሻ ምርኮኛ እየሆነ እንደሚገኝ አስታውቀዋል።

መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ለሰራዊቱ እያሳየ ያለው ድጋፍ ከፍ ያለ የሞራል ልእልና እንዳላበሰውም አስታውቀዋል።

ለኢትዮጵያ ነቀርሳ የሆነውን ከሀዲ ቡድን በመደምሰስ የሕግ የበላይነትና ህገመንግስታዊ ስርዓት ለማረጋግጥ በብቃት እየተሰራ መሆኑን አዲስ ዘመን ዘግቧል።

የመከላከያ ኃይሉ ሕዝብ እንዳይጎዳ ለማድረግ ሕዝብ እና ጽንፈኛ ኃይሉን ለይቶ ለመምታት በጥንቃቄ እየተንቀሳቀሰ መሆኑንም ጄኔራል ብርሃኑ ተናግረዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.