Fana: At a Speed of Life!

ዳያስፖራው በጫና ኢኮኖሚው እንዳይዳከም ድጋፍ ለማድረግ መዘጋጀቱን አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ጦርነት እና በውጭ ሀይሎች ጫና የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ እንዳይዳከም ቀጣይነት ባለው መልኩ የገንዘብ ድጋፍ ለማድረግ መዘጋጀታቸውን ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ገለጹ።

በአሜሪካ እና አውሮፓ የሚኖሩት የዳያስፖራ ማህበረሰብ አባላት በበይነ መረብ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ባደረጉት ቆይታ፥ ወደ አገር ቤት የሚልኩትን የውጭ ምንዛሬ ህጋዊ መንገድ በመከተል እና በተለያዩ ስልቶች የአገርን ኢኮኖሚ ለመደገፍ እንሰራለን ብለዋል።

በሽብር ቡድኑ ከቀያቸው ተፈናቅለው ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ከ150 ሺህ የአሜሪካ ዶላር በላይ ከአምስት ወራት በፊት ባቋቋሙት በጎ አድራጎት ማህበር፥ ወደ ኢትዮጵያ መላካቸውን በአሜሪካ ሲያትል ነዋሪው ኢንጂነር ሲሳይ አለማየሁ ተናግረዋል።

በአሜሪካ ዘዋሪነት ያልተገባ እና ያልተቋረጠ ጫና በኢትዮጵያ ላይ እየተፈጸመ በመሆኑ የአገር ኢኮኖሚ እንዳይጎዳ በሰላማዊ ሰልፍ እና በዲፕሎማሲው ያደረጉትን ድጋፍ በኢኮኖሚ ለመድገም እንቅስቃሴ እያደረጉም ይገኛሉ ብለዋል።

ሌላኛው በአሜሪካ ሲያትል ነዋሪው ትውልደ ኢትዮጵያዊው የህክምና ባለሙያው ግርማቸው ተፈራ ከዚህ ቀደም 200 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ከአማራ እና አፋር ክልሎች ለተፈናቀሉ ወገኖች ማህበራቸው ድጋፍ ማድረጉን ገልጸዋል።

ጦርነቱ ዘርፈ ብዙ እና የአገርን ኢኮኖሚ ለማድቀቅ የተነሳ በመሆኑ ወደ አገር ቤት የሚልኩትን የውጭ ምንዛሬ ህጋዊ መንገድ በመከተል እንዲሆን የማድረግ ዘመቻም ጀምረናል ነው ያሉት።

ይህን የምናደርገው በአገር ውስጥ ያለው መንግስት ህዝብ የመረጠው እና በውጪ የሚኖሩ ኢትዮጵያውን በመንግስታቸው ከምንም ጊዜ በላይ መተማመን የፈጠሩበት መሆኑ አንስተዋል።

በብራሰልስ ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ ተመራማሪው ዶክተር ዘሪሁን አሰፋ፥ የአገር ኢኮኖሚ ጫናን ለመቋቋም እውቀት እና ሙያን ጨምሮ በተለያዩ ስልቶች ኢኮኖሚውን ለመደገፍ እንሰራለን ብለዋል።

በኢትዮጵያ ላይ በሀሰት ፕሮፖጋንዳ ተጽዕኖ የሚፈጥሩ የምዕራባውያን መገናኛ ብዙሃንን ከፍለው ባለመጠቀም እና ደንበኝነታቸው በማቋረጥ ለመቅጣት የሚያሰችል ዘመቻ መጀመራቸውንም ኢትዮጵያውያኑ ይናገራሉ።

በበላይ ተስፋዬ

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.