Fana: At a Speed of Life!

ዳያስፖራዎች ወደ አገራቸው ሲመጡ የሥራ ፈጠራ ልማትን እንዲያግዙ ጥሪ ቀረበ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ወደ አገራቸው ሲመጡ የሥራ ፈጠራ ልማትን እንዲያግዙ የሥራ እና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ጥሪ አቅርበዋል፡፡
 
ሚኒስትሯ ይህንን ጥሪ ያቀረቡት አንድ ሚሊየን ለሚሆኑ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በጠቅላይ ሚኒስትሩ የቀረበውን ጥሪ ተከትሎ ነው፡፡
 
በአገራችን የተጀመረውን አገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርም በመጥቀስ በዲጂታል ኢንተርፕርነርሺፕ ሥራዎች ውጤት ያመጡ ኢትዮጵያውያን መኖራቸውንም ሚኒስትሯ ገልፀዋል።
 
“የኢንተርፕርነርሺፕ ልማት እንቅስቃሴ ዘግይተን የገባንበት የሥራ መስክ ቢሆንም ሰፊ ዕድል ያለውና ቅድሚያ የምንሰጠው በመሆኑ ያላችሁን ዕውቀት እና ክህሎት በኢትዮጵያ ለሚገኙ እህት እና ወንድሞቻቸሁ ከማካፈል ጀምሮ በመስኩ በተናጠልም ሆነ ተደራጅታችሁ መሰማራት ብትችሉ እንደ አገር የጀመርነውን የኢኮኖሚ ግንባታ ሥራ በፅኑ መሠረት ላይ በማቆም ረገድ ትልቅ አሻራ ማሳረፍ ስለምትችሉ ልንቀበላችሁ ዝግጁ ነን ” ማለታቸውን ከስራ እና ክህሎት ሚኒስትቴር ያገኘነው መረጃ ያለመክታል፡፡
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.