Fana: At a Speed of Life!

ዳያስፖራዎች የአሜሪካ አቋምን የማስቀየር አቅም አላቸው – ወ/ሮ ሶስና ወጋየሁ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 6፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ)የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ማኅበራት ጥምር ሰብሳቢ ወይዘሮ ሶስና ወጋየሁ÷ ለአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን መመረጥ ከ800 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ከፍተኛ አስተዋጽኦ ነበራቸው ሲሉ ገለፁ፡፡

ሰብሳቢዋ÷ ትውልደ ኢትዮጵያዊያኑ አሁን ላይ ሀገራችን በባይደን አስተዳደር ጫና እየደረሰባት መሆኑን ይገነዘባሉ፤ ስለሆነም የሀገራቸውን እውነታው ለዓለሙ ማኅበረሰብ ለማስረዳት በጥምረት መንቀሳቀሰ አለባቸው ብለዋል፡፡

ፕሬዚዳንቱ የኢትዮጵያዊያኑን ዳያስፖራ ድምጽ ባያገኙ ኖሮ ወደ ስልጣን ላይመጡ ይችል እንደነበርም ገልጸዋል፡፡

በመሆኑም ለባይደን ድምጽ የሰጡት ኢትዮጵያዊያንና ትውልድ ኢትዮጵያውያኑ የአሜሪካን መንግስት አቋም የማስቀየር በቂ ምክንያትና አቅም እንዳላቸውም አውቀው በጥምረት ሊንቀሳቀሱ ይገባል ማለታቸውን የዘገበው ኢፕድ ነው፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.