Fana: At a Speed of Life!

ድል ያለ መሥዋዕትነት አይገኝም-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 14 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ድል ያለ መሥዋዕትነት እንደማይገኝ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ተናገሩ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በህግ ማስከበር ዘመቻ ጉዳት ካጋጠማት ወታደር ዓለሚቱ አምባ ጋር ቆይታ አድርገዋል፡፡
ቆይታቸውን አስመልክተው በትዊተር ገፃቸው ባስተላለፉት መልዕክት ድል ያለ መሥዋዕትነት እንደማይገኝ አንስተዋል፡፡
ጀግናው ሠራዊታችን የሀገራችንን ክብር፣ ነጻነት እና ሉዓላዊነት የሚያስከብረው የላብና የደም ዋጋ ከፍሎ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ÷ ይሄንን ተመን የማይገኝለት ዋጋ ሲከፍል ደግሞ ሕዝብ እና መንግሥት ከጎኑ መቆም አለባቸው ብለዋል፡፡
እንደ ወታደር ዓለሚቱ አምባ ያሉ በሕግ ማስከበር ዘመቻ ወቅት የተጎዱ የሠራዊት አባላት ለጀግንነታቸው የሚመጥን ክብካቤና ድጋፍ እንዲያገኙ እየሠራን ነው ነው ያሉት፡፡
የሕክምናና የሰው ሠራሽ አካል ድጋፍ ማድረጊያ ማዕከላትን እያጠናከርን ነው፤ ማህበራዊ ሕይወታቸውን ለመደገፍ የሚያስችል ሥራም እየሠራን ነው ብለዋል፡፡
ኢትዮጵያ ለእነርሱ የማትሆነው የለም ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.