Fana: At a Speed of Life!

ድሬዳዋ ለቁልቢ ገብርኤል ዓመታዊ የንግስ በዓል እንግዶችን ለማስተናገድ ተዘጋጅታለች

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የድሬዳዋ አስተዳደርና ህዝቡ ለቁልቢ ገብርኤል ዓመታዊ የንግስ በዓል ዳያስፖራውን ጨምሮ የሚመጡ እንግዶችን ተቀብለው ለማስተናገድ ዝግጁ መሆናቸው ተገለጸ።
የአስተዳደሩ ከንቲባ ከድር ጁሃር አስተዳደሩና ህዝቡ ለቁልቢ ገብርኤል ዓመታዊ የንግስ በዓል የሚመጡ የድሬዳዋ ተወላጆች፣ወዳጆች፣ ዳያስፖራዎችና ሌሎችንም እንግዶች ተገቢው አቀባበልና መስተንግዶ እንደሚጠብቃቸው ጠቁመዋል።
እንግዶችን በሰላም ተቀብለን በሰላም እንዲመለሱ ዝግጅታችን ተጠናቋል ብለዋል ከንቲባው።
የድሬዳዋ ፖሊስ ኮሚሽነር አለሙ መግራ በበኩላቸው፥ የፀጥታ አካላት የዘንድሮ የቁልቢ ገብርኤል ዓመታዊ የንግስ በዓል በሰላም እንዲከበር ከመቼውም ጊዜ በላይ ዝግጅት ማድረጋቸውን ተናግረዋል።
የድሬዳዋ፣ የሐረሪ፣ የምስራቅና የምዕራብ ሐረርጌ ዞኖች፣ የፌደራል ፖሊስ፣ ሚሊሻና ብሔራዊ ደህንነት ለበዓሉ ሰላምና ደህንነት መጠበቅ ተቀናጅተው እየሰሩ መሆኑንም አመላክተዋል፡፡
ከውጭ ወደ ሀገር ቤት የሚገቡትንና ለበዓሉ ከተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች የሚመጡትን እንግዶች ህዝቡ በተለመደው የእንግዳ ተቀባይነት ባህል እንዲያስተናግድ ጥሪ አቅርበዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።
ታህሳስ 19 በሚከበረው የቁልቢ ገብርኤል የንግስ በዓል ለመታደም ምዕመናን፣ ጎብኚዎች፣ አምባሳደሮች እና ዳያስፖራዎች እንደሚገኙ ይጠበቃል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.