Fana: At a Speed of Life!

ድርጅቱ በትግራይ ክልል ለተፈናቀሉ ዜጎች ለጊዜያዊ መጠለያ የሚውል የፕላስቲክ ሸራ እና በጸሐይ ሃይል የሚሰሩ አምፖሎች ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 21 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ሳማሪታንስ ፐርስ የተባለ ግብረ ሰናይ ድርጅቱ በትግራይ ክልል ለተፈናቀሉ ዜጎች ከስምንት ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያለው ለጊዜያዊ መጠለያ የሚውል የፕላስቲክ ሸራ እና በጸሐይ ሃይል የሚሰሩ አምፖሎችን ድጋፍ አደረገ፡፡
ሳማሪታንስ ፐርስ የተባለው ድርጅት ከዋናው መስሪያ ቤት አሜሪካ ኖርዝ ካሮላይና – ቡን ከተማ በራሱ የዕቃ ጫኝ አውሮፕላን የላከው ቁሳቁስ በዛሬው ዕለት መቀሌ አሉላ አባ ነጋ አየር ማረፊያ ደርሷል፡፡
ድጋፉንም የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶክተር ሙሉ ነጋ እና ሌሎች የካቢኔ አባላት ተረክበዋል።
ድርጅቱ ከዋና መስሪያ ቤቱ ኖርዝ ካሮላይና ስቴት የላከው ለሁለት ሺህ ሰዎች ለመጠለያነት የሚውል የፕላስቲክ ሸራ እና አምስት ሺህ በጸሐይ ሃይል የሚሰሩ አምፖሎችን መሆኑ ታውቋል፡፡
ቁሳቁሶቹም በህግ ማስከበር ሂደቱ ከቀዬአቸው ለተፈናቀሉ እና የአስቸኳይ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች የሚውል ነው ተብሏል፡፡
ግብረ ሰናይ ድርጅቱ ባሳለፍነው ጊዜ በትግራይ ክልል ሰብዓዊ ድጋፍ ለሚያሥፈልጋቸው እናቶችና ህጻናት የሚውል ከ30 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያለው አልሚ ምግብ ድጋፍ ማድረጉ ይታወሳል፡፡
ሰማሪታንስ ፐርስ በኢትዮጵያ በበጎ አድራጎት ምዝገባ ቁጥር 4046 ተመዝግቦ የበጎ አድራጎት ስራ በማከናወን ላይ እንደሚገኝ ከግብረ ሰናይ ድርጅቱ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-

https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.