Fana: At a Speed of Life!

ዶናልድ ትራምፕ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ህንድ ገቡ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 16፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለመጀመሪያ ጊዜ ይፋዊ የስራ ጉብኝት ለማድረግ ህንድ ገቡ።

ፕሬዚዳንቱ ህንድ ሲደርሱ የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ለሁለት ቀናት ጉብኝት ህንድ የገቡት ፕሬዚዳንቱ አህመዳባድ ከተማ ሲደርሱ በርካታ ህንዳውያን ጎዳና ላይ በመውጣት አቀባበል ያደረጉላቸው ሲሆን፥ በቀጣይም በጉጅራት ግዛት በሚገኘው የክሪኬት ስታድየም ህዝባዊ አቀባበል ይደረግላቸዋል ተብሏል።

ፕሬዚዳንቱ በቆይታቸው የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ማጠናከር በሚቻልበት ጉዳይ ላይ ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ትራምፕ ከጠቅላይ ሚኒስትር ሞዲ ጋር 100 ሺህ ሰዎች በተገኙበት ህዝባዊ የአቀባበል ስነ ስርዓት ላይ ንግግር እንደሚያደርጉም ነው የሚጠበቀው።

ምንጭ፡- ቢቢሲ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.