Fana: At a Speed of Life!

ዶናልድ ትራምፕ በምርጫው መሸነፋቸውን ሊቀበሉ እንደሚችሉ ፍንጭ ሰጡ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 18፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በምርጫው መሸነፋቸውን ሊቀበሉ እንደሚችሉ ተናገሩ፡፡

ፕሬዚዳንት ትራምፕ በምርጫው በጆ ባይደን መሸነፋቸውን አምነው ሊቀበሉና ነጩን ቤተ መንግስት ሊለቁ እንደሚችሉ ፍንጭ ሰጥተዋል፡፡

ፕሬዚዳንቱ ከጋዜጠኞች ጋር በነበራቸው ቆይታ ጆ ባይደን በኤሌክቶራል ኮሌጅ ቀጣዩ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት መሆናቸው ከተረጋገጠ ሽንፈታቸውን ሊቀበሉ እንደሚችሉ ጠቅሰዋል፡፡

ይሁን እንጅ ኤሌክቶራል ኮሌጁ ይህን ካደረገ ስህተት ሰርቷልም ብለዋል፡፡

ሽንፈታቸውን ለመቀበል ያቅማሙት ትራምፕ የምርጫ ውጤቱን ለመቀበል በጣም ከባድ ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

ከሶስት ቀን በፊት ትራምፕ ተመራጩ ባይደን አዲሱን አስተዳደራቸውን መመስረት እንዲጀምሩ በይፋ እውቅና መስጠታቸው ይታወሳል፡፡

የግዛት ወኪሎች በቀጣዩ ወር ተገናኝተው በምርጫው መራጮች የሰጡትን ድምጽ ለተመራጩ ፕሬዚዳንት በመስጠት አጠቃላይ ውጤቱን የሚወስኑ ይሆናል፡፡

ተመራጩ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደንም በፈረንጆቹ ታህሳስ 20 ቀን አዲሱ ፕሬዚዳንት በመሆን ቃለ መሃላ ይፈጽማሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በአሜሪካ ህግ መሰረት መራጮች ድምጻቸውን በቀጥታ ለፕሬዚዳንቱ ሳይሆን ለየግዛት ተወካዮች ይሰጣሉ፡፡

የየግዛት ወኪሎችም በሚኖራቸው የህዝብ ብዛት የሚወሰን ይሆናል፡፡

በፕሬዚዳንታዊ ምርጫው ጆ ባይደን 306 ኤሌክቶራል ቮት ሲያገኙ በአንጻሩ ፕሬዚዳንት ትራምፕ 232 ድምጽ አግኝተዋል፡፡

 

ምንጭ፡-ቢቢሲ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.