Fana: At a Speed of Life!

ዶናልድ ትራምፕ ቲክቶክ በአሜሪካ ሊታገድ ይችላል ማለታቸውን ተከትሎ ማይክሮሶፍት ከኩባንያው ጋር ሲያደርግ የነበረውን ድርድር አቋረጠ

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 26፣ 2012(ኤፍ ቢ ሲ) የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በትናትናው ዕልት ቲክቶክ መተግበሪያ ከአሜሪካ ሊታገድ ይችላል ማለታቸው የሚታወስ ነው።

የአሜሪካው የቴክኖሎጂ ኩባንያ የሆነው ማይክሮሶፍት የቲክቲኮን የአሜሪካ ድርሻን ለመግዛት ከባይትዳንስ ከተሰኘው የቻይና የቴክኖሎጂ ኩባንያ ጋር ድርድር ላይ ነበር።

ሆኖም ዶናልድ ትራምፕ ግዙፉ የቲክቶክ አገልግሎት ሊቋረጥ ይችላል ማለታቸውን ተከትሎ ማይክሮሶፎት እና ባይትዳንስ ሲያደርጉት የነበረው ድርድር መቋረጡ ነው የተነገረው።

የተወሰኑ የአሜሪካ ፓለቲከኞች ቲክቶክ የአሜሪካ ዜጎችን የግል መረጃ አሳልፎ በመስጠት የደህንነት ችግር ሊፈጥር ይችላል ሲሉ ስጋታቸውን ሲገልፁ ቆይተዋል።

ኩባንያው በበኩሉ የአሜሪካውያን መረጃዎች በአሜሪካ የመረጃ ቋት ብቻ የሚቀመጡ በመሆኑ ስጋት ሊኖር አይገባም በማለት የሚቀርብበትን ክስ አጥጥሏል።

ቲክቶክ በዓለም አቀፍ ደረጃ 500 ሚሊየን ደንበኞች እንዳሉት የሚነገር ሲሆን 80 ሚሊየኖቹ ደግሞ አሜሪካ ውስጥ የሚገኙ ደንበኞች መሆናቸውን የቢቢሲ ዘገባ ያመለክታል።

ቲክቶክ አጫጭር ቪዲዮት ማጋራት አገልግሎት የሚሰጥ ማህበራዊ ሚዲያ አገልግሎት ነው።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.