Fana: At a Speed of Life!

ዶናልድ ትራምፕ የግላቸውን የማህበራዊ ትስስር ገፅ ይዘው ሊመጡ ነው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 13፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሜሪካው የቀድሞው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የግላቸውን ማህበራዊ ትስስር ገፅ ይዘው ሊመጡ መሆኑን አማካሪያቸው አስታውቀዋል።

አማካሪያቸው ጀሶን ሚለር ዶናልድ ትራምፕ በሁለት እና ሶስት ወራት ውስጥ ወደ ማህበራዊ የትስስር ገፅ ይመለሳሉ ብየ አስባለሁ ብለዋል።

ዶናልድ ትራምፕ ይዘውት የሚመጡት ማህበራዊ  የትስስር ገፅ እጅግ ተፈላጊና ጨዋታውን ሙሉ በሙሉ የሚቀይር  ይሆናል ሲሉም ነው አማካሪያቸው የተናገሩት።

ትራምፕ ባለፈው ጥር ወር ደጋፊዎቻቸው በካፒቶል ሂል ሁከት መፍጠራቸውን ተከትሎ ከፌስቡክና ከትዊተር ማህበራዊ የትስስር ገፅ መታገዳቸው የሚታወስ ነው።

በካፒቶል ሂል የተፈፀመው ጥቃት የአምስት ሰዎች ህይወት ማለፍእና በአሜሪካ የዴሞክራሲ መሰረት ላይ ጥያቄ እንዲነሳ ያደረገ ነበር።

ላለፉት አስርት ዓመታት ከዋነኞቹ  መገናኛ ብዙሃን ይልቅ ማህበራዊ ትስስር ገፅን ከደጋፊዎቻቸው ጋር ለመገናኘትና መረጃዎችን ለማሰራጨት ሲጠቀሙ የነበሩት ዶናልድ ትራምፕ እገዳው ክፉኛ እንደጎዳቸው ይነገራል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.