Fana: At a Speed of Life!

ዶክተር ቴድሮስና ትውልደ ኢትዮጵያዊው አርቲስት አቤል ተስፋዬ( ዘ ዊክንድ) የ2020 100 ተፅዕኖ ፈጣሪዎች መካከል ተካተቱ

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 13 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአለም ጤና ድርጅት ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም እና ትውልደ ኢትዮጵያዊው አለም አቀፍ ድምፃዊ አቤል ተስፋዬ (ዘ ዊክንድ) በ2020 የታይም መፅሄት 100 ተፅዕኖ ፈጣሪዎች ውስጥ ተካታቱ።
ዶክተር ቴድሮስ በመሪዎች ዘርፍ እንዲሁም ድምፃዊ አቤል ተስፋዬ (ዘ ዊክንድ) በአርቲስቶች ዘርፍ ከ100 ተፅዕኖ ፈጣሪዎች መካከል መካተታቸው ታውቋል።
የአለም ጤና ድርጅት ዋና ስራ አስፈፃሚ የሆኑት ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም በየትኛው የአለም ክፍል የሚገኝ ማንኛውም ሰው ጥራት ያለው የጤና እንክብካቤ ማግኘት አለበት የሚል ጠንካራ አቋም እንዳላቸው መፅሄቱ አንስቷል።
በሀገራቸው ኢትዮጵያ በቁጥጥር ስር ሊውሉ የሚችሉ በሽታች የሰዎችን ህይወት ሲቀጥፉ በልጅነታቸው ያዩት ዶክተር ቴድሮስ በዲሞክራቲክ ኮንጎ በተከሰተው የኢቦላ ወረርሽኝ ምላሽ ላይ በግል ሃላፊነታቸውን መወጣታቸውን ተጠቁሟል።
ይህም በአለም አቀፍ ደረጃ የተከሰተው የኮሮና ቫይረስን መከላከል ላይ ተስፋና እና ጠንካራ ዓለማ እንዲኖራቸው አስችሏል ብሏል መፅህሄቱ።
ሌላኛው ተፅዕኖ ፈጣሪ ትውልደ ኢትዮጵያዊ የካንዳ ዜግነት ያለው አቤል ተስፋዬ ( ዘ ዊክንድ ) በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳጅነትን እያተረፈ የመጣ ድምፃዊ፣ ገጣሚ እና የሙዚቃ ፕሮዲውሰር ነው።
አቤል ተስፋዬ (ዘ ዊክንድ ) በ2020 በለቀቀው after hours በተሰኘ የሙዚቃ አልበም ተወዳጅነትን ማግኘት የተነገረ ሲሆን በተለይ Blinding Lights ሙዚቃው በ2020 በፖፕ ሙዚቃ ዘርፍ ተመራጪ መሆኑን መረጃዎቹ ያመለክታሉ።
በተመሳሳይ ሌላኛዋ ኢትዮያዊት ሰዓሊ ጆሊ ምህረቱ በታይም መፅሄት የ2010 ተፅዕኖ ፈጣሪዎች መካከል ተካታለች።

በሌላ ዜና የ2020 “ብሪጅ ሜከር አዋርድ” አሸናፊ የሆኑት ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም ሽልማታቸውን በትላንትናው እለት ተቀብለዋል።

ሽልማቱ ኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከል ግንባር ቀደም ሆነው እያገለገሉ ላሉ የጤና ባለሙያዎች መታሰቢያ ይሁንልኝ ሲሉ የምስጋና መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.