Fana: At a Speed of Life!

ዶ/ር ሊያ ታደሰ በማይጠብሪ ግንባር በህወሓት የወደሙ የጤና ተቋማትን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 15፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ በሰሜን ጎንደር ዞን በሽብር ቡድኑ ህወሓት የወደሙ የጤና ተቋማትን እና የተፈናቀሉ ዜጎችን ጎብኝተዋል።
የአሸባሪው ህወሓት ቡድን በአማራ እና አፋር ክልሎች በተለያዩ አካባቢዎች ህጻናት እና ሴቶችን ጨምሮ በርካታ ንጹሃን ዜጎችን ጨፍጭፏል።
ከዚህ ባለፈም ቡድኑ በወረራ ይዟቸው በነበሩ አካባቢዎች የጤና ተቋማትን እና በርካታ መሠረተ ልማቶችን አውድሟል።
የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰም በሰሜን ጎንደር ዞን አዲ ዓርቃይ ወረዳ በሽብር ቡድኑ የወደመውን የዛሪማ ጤና ጣቢያ ጎብኝተዋል።
የትህነግ ወራሪ ሃይል 42 ሺህ ዜጎች ይገለገሉበት የነበረውን የዛሪማ ጤና ጣቢያ ሙሉ በሙሉ አውድሟል።
አሁን ላይም ጤና ጣቢያው ምንም አይነት አገልግሎት የማይሰጥ በመሆኑ የአካባቢው ነዋሪዎች ለከፋ ችግር ተዳርገዋል።
ሚኒስትሯ በሽብር ቡድን ከሰሜን ጎንደር ዞን የተለያዩ አካባቢዎች የተፈናቀሉ ዜጎችንም ጎብኝተዋል።
ሚኒስትሯ በዞኑ በሽብር ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች አገልግሎት እየሰጠ የሚገኘውን የደባርቅ ሆስፒታልንም ጎብኝተዋል።
በሽብር ቡድኑ የወደሙ የጤና ተቋማትን መልሶ ስራ ለማስጀመርም የጤና ሚኒስቴር ከአጋር አካላት ጋር በቅንጅት እየሰራ መሆኑን ደ/ር ሊያ ተናግረዋል።
በመላኩ ገድፍ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
+8
81,049
People Reached
4,931
Engagements
Boost Post
1.5K
36 Comments
50 Shares
Like

Comment
Share
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.