Fana: At a Speed of Life!

ዶ/ር ሊያ ታደሰ በእስራኤል የፓርላማ አባል እና በኢትዮ-እስራኤል የፓርላማ ወዳጅነት ማህበር ሊቀመንበር ከተመራው ልዑክ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ በእስራኤል የፓርላማ አባል እና በኢትዮ-እስራኤል የፓርላማ ወዳጅነት ማህበር ሊቀመንበር ጋዲ ይቫርካን የሚመራና ሌሎች የፖርላማ አባላት፣ ከተለያዩ የሕክምና ተቋማት የተወጣጡ አመራሮችን ከያዘው የልዑካን ቡድን ጋር ተወያዩ፡፡
ውይይቱን አስመልክቶ ሚኒስትሯ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው÷ ከልዑኩ ጋር በኢትዮጵያ ጦርነት በተከሰተባቸው አካባቢዎች የሰብአዊ ድጋፍና መልሶ ለማቋቋም በሚደረገው ጥረት በጋራ መስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ መምከራቸውን አስፍረዋል፡፡
በተጨማሪም ከእስራኤል መንግስት እና የህክምና ተቋማት ጋር ያለውን አጋርነት በማጠናከር የስፔሻሊቲ ህክምናዎች ከማጠናከር አኳያ የአቅም ግንባታ ስራዎችን ከዩኒቨርስቲ ሆስፒታሎች ጋር በመስራት በተለይም የልብ እና የቀዶ ህክምና ፣ የድንገተኛ እና የአደጋ ህክምና እና ሌሎች ጉዳዮች ላይ በጋራ መሰራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ መወያየታቸው ተገልጿል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.