Fana: At a Speed of Life!

ዶ/ር ሊያ ታደሰ ከአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አገኘሁ ተሻገር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ የተመራው ልዑክ ከአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አገኘሁ ተሻገርና ከሌሌች የክልሉ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ጋር ተወያዩ፡፡

ልዑኩ በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ዞን የህወሃት የጥፋት ቡድን ባደረሰው ጉዳት የተፈናቀሉ ወገኖችንና የወደሙ የጤና ተቋማትን ተመልክቷል።

በውይይቱ በሰሜን ጎንደር ከወደሙት ጤና ተቋማት አንዱ የሆነው ዛሪማ ጤና ጣቢያ ስራ አለመጀመሩ፣ የደባርቅ እና ጎንደር ሆስፒታሎች ጫናዎችን ተቋቁመው አየሰሩ መሆናቸው የተነሳ ሲሆን ÷በዞኑ ከ26 ሺህ በላይ የሚሆኑ ተፈናቃይ ወገኖች የተለያዩ ድንገተኛ ህክምና አገልግሎትና ሌሎች ድጋፎች እንደሚያስፈልጋቸው ተገልጿል።

የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድ አቶ አገኘሁ ተሻገር÷የጤና ሚኒስቴር እያደረገ ላለው እገዛ አመስግነው ክልሉ ቁስለኞችንና ተፈናቃዮችን ለመደገፍ የተቻለውን እያደረገ ቢሆንም በተለይ የጤና መሰረተ ልማት መልሶ ለማቋቋም ሁሉም አካላት እንዲረባረቡ ጠይቀዋል።

የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ በበኩላቸው÷ ባለፉት ሶስት ወራት ለድንገተኛ ምላሽ በጉዳቱ የተፈናቀሉ ወገኖች የሚውል 217 ነጥብ 6 ሚሊየን ብር የሚያወጡ የህክምና ግብኣቶች፣ መድሃኒቶችና መሳሪያዎች እንዲሁም የገንዘብ ድጋፍ መደረጉ ገልፀዋል፡፡

በቀጣይም ከሚመለከታቸው የፌዴራልና ክልሉ አካላት ጋር በመሆን የመልሶ ማቋቋም ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል መናገራቸውን ከጤና ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.