Fana: At a Speed of Life!

ዶ/ር ሊያ ታደሰ የኮቪድ 19 ክትባትን ለ92 ሀገራት ተደራሽ ለማድረግ በአስተባባሪነት ተመረጡ

አዲስ አበባ፣ ጥር 5፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ የኮቪድ 19 ክትባትን ተደራሽ ለማድረግ በሚሰራው አለም አቀፍ የንቅናቄ ቡድን ውስጥ በአስተባባሪነት ተመረጡ፡፡
የንቅናቄ ቡድኑ በአለም አቀፉ የጤና ድርጅት እና የክትባት ትብብር የሚመራ ሲሆን የኮሮናቫረስ ክትባት ለሁሉም ሀገራት በፍትሀዊነት ተደራሽ እንዲሆን የሚሰራ ነው፡፡
በቡድኑ አስተባባሪ ሆነው የተመረጡት የኢፌዴሪ ጤና ሚኒስቴር ዶክተር ሊያ ታደሰ፣ የኢንዶኔዢያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሬትኖ ማርሱዲ እና የካናዳ የአለም አቀፍ የልማት ሚኒስትር ካሪና ጉልድ ናቸው፡፡
ቡድኑ እንዳስታወቀው የቫረሱ ክትባት ዝቅተኛ እና መካከለኛ ገቢ ላላቸው 92 የአለማችን ሀገራት ተደራሽ የሚሆን ነው፡፡
በቡድኑ በኩልም ክትባቱ ከለጋሽ ሀገራት በመሰብሰብ ለ92 ሀገራት በፍትሀዊነት የሚከፋፈል ይሆናል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.