Fana: At a Speed of Life!

ዶ/ር ታደሰ ካሳ የሚኒስትሮች ግብረ-ሃይል ጽ/ቤት ኃላፊ ሆነው ተሸሙ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 5 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በትግራይ፣ አማራና አፋር ክልሎች የተፈፀሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ለመመርመር፣ ጥፋተኞችን በህግ ተጠያቂ ለማድረግና ተጎጂዎችን መልሶ ለማቋቋም የተመሰረተው የሚኒስትሮች ግብረ-ሃይል ዶ/ር ታደሰ ካሳን የግብረ-ሃይሉ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አድርጎ መሾሙን አሳውቋል፡፡
 
መንግስት በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል በዜጎች ላይ የደረሰውን የሰብዓዊ መብት ጥሰት በተመለከተ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር ጽህፈት ቤት እና የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን በጥምረት በካሄዱት የምርመራ ውጤት ሪፖርት ላይ የተመላከቱ ምክረ ሀሳቦችን በጥልቀት አይቶ ምላሽ ለመስጠት የሚኒስትሮች ግብረ-ሃይል በማቋቋም እንዲሁም የተጠቃለለ ስትራቴጂ እና ዝርዝር የድርጊት መርሃ ግብር በማዘጋጀት ወደ ሥራ መገባቱ ይታወሳል።
 
ግበረ-ሃይሉ በዋናነት በተመድ የሰብዓዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር ጽ/ቤት እና በኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ጥምር የምርመራ ቡድን ግኝትና ምክረ-ሀሳብ ላይ በመመስረት በትግራይ፣ አማራና አፋር ክልሎች የተፈፀሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን የመመርመርና አጥፊዎችን ተጠያቂ የማድረግ እንዲሁም ተጎጂዎችን መልሶ የማቋቋም ኃላፊነት ተሰጥቶትና አራት ኮሚቴዎች ተዋቅረው ወደ ሥራ ተገብቷል፡፡
 
አጠቃላይ የግብረ-ሃይሉ ሥራዎች ማለትም የወንጀል ምርመራና ክስ ሥራው በፍትሕ ሚኒስቴር ሰብሳቢነት የመከላከያ ሚኒስቴር፣ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን እንዲሁም የክልል ፖሊስና ፍትሕ ቢሮዎች የሚተገበር ሲሆን፥ የስደተኞችንና ተፈናቃዮች ጉዳይ የማጣራቱ ሥራ በሰላም ሚኒስቴር ሰብሳቢነት በስደተኞችና ከስደት ተመላሾች ጉዳይ ኤጀንሲ፣ በብሔራዊ የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽንና በክልል መስተዳድሮች የሚተገበር ነው።
 
የተፈጸሙ ፆታዊ ጥቃቶችን የማጣራቱ ሥራ በሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሰብሳቢነት በፍትሕ ሚኒስቴር፣ በጤና ሚኒስቴር፣ በፌደራል ፖሊስ ኮሚሽንና በክልል ፍትሕ ቢሮዎች እንደሚተገበር ነው ከፍትህ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ የሚጠቁመው።
 
እንዲሁም የሀብት ማሰባሰብ ሥራው ደግሞ በገንዘብ ሚኒስቴር ሰብሳቢነት በፍትሕ ሚኒስቴር፣ በጤና ሚኒስቴር፣ በሰላም ሚኒስቴርና በብሔራዊ የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ይተገበራል።
 
ፅህፈት ቤቱ በተለይም የግብረ- ሃይሉንና በስሩ የተዋቀሩ ኮሚቴዎች ዕቅድና አጠቃላይ እንቅስቃሴ በመከታተልና የተለያዩ የመገናኛ ዘዴዎችን በመጠቀም መረጃ የማድረስና ሌሎች የተሰጡት ኃላፊነቶችን የሚወጣ ስለመሆኑ ነው የተገለፀው።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.