Fana: At a Speed of Life!

ዶ/ር አብረሃም በላይ ከህንድ አምባሳደር ሽሪ ሮበርት ሸቲቶንግ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 6 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚንስትር ዶክተር አብርሀም በላይ በኢትዮጵያ የህንድ አምባሳደር ሽሪ ሮበርት ሸቲቶንግ ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል።
ውይይታቸው በኢትዮጵያና ህንድ ትብብር በአዲስ አበባ የሚገነባው የአይሲቲ ሴንተር ግንባታ እና ኢትዮጵያ በፓን አፍሪካ ኢ-ኔትዎርክ ተሳታፊ በምትሆንበት መንገድ ዙርያ ያተኮረ ነው።
ከዚያም ባለፈ በኢትዮጵያ እና ህንድ መካከል ከዚህ በፊት በአይሲቲ፣ በሰው ሀይል ግንባታ እና በተለያዩ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ዘርፎች ከዚህ ቀደም በጋራ ለመስራት የተስማሙባቸው ጉዳዮች ተግባራዊ በሚደረግበት ዙርያም ተወያይተዋል።
በኢትዮ ህንድ ትብብር በአዲስ አበባ የአይሲቲ ማእከል ለማቋቋም የተደረገው ስምምነት በቅርቡ ወደ ስራ እንዲገባም መግባባት ላይ መድረሳቸውንከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.