Fana: At a Speed of Life!

ጁንታው በሑመራ ከተማ የማይካድራ ዓይነት ጭፍጨፋ ለመፈጸም ያሰበው ዕቅድ ተጋልጧል – የመረጃ ማጣሪያ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 15 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የህወሃት ጁንታ የማይካድራ ዓይነት ጭፍጨፋ በሑመራ ከተማ ለመፈጸም ያሰበው ዕቅድ ማፈትለኩን የወቅታዊ ሁኔታ የመረጃ ማጣሪያ አስታወቀ፡፡
በዕቅዱ መሠረት ከትግራይ ክልልና ከሱዳን አስርጎ በሚያስገባቸው ሠርጎ ገቦች አማካኝነት ጭፍጨፋውን እንደሚፈጽም ገልጿል።
ይሄንን ለማድረግ እንዲመች በራያና አፋር በኩል ተደጋጋሚ ትንኮሳ በመፈጸም የመከላከያ ሠራዊቱንና የአማራ ክልል ልዩ ኃይልን ትኩረት የማዛባት እቅድ እንዳለውም ነው ያስታወቀው።
የጦሩ ኃይል ወደ ራያና አፋር ሲሰባሰብና የምዕራቡ ኃይል ሲሳሳ በዚያ በኩል ጥቃት በመክፈት ድርጊቱን ለመፈጸም ማቀዱንም የወቅታዊ ሁኔታ የመረጃ ማጣሪያ ገልጿል፡፡
ጁንታው ከሰሞኑ የአማራ ልዩ ኃይልና መከላከያ በሑመራ ጭፍጨፋ እንደሚፈጽሙ በማህበራዊ ሚዲያ ማሠራጨት እንደሚጀምር ዕቅዱ ያሳያልም ነው ያለው።
በሌላ በኩል ጁንታው ከሰሞኑ በአፋር ግንባር በፈጠረው ትንኮሳ ከአፋር ልዩ ኃይልና ከመከላከያ ሠራዊት ምላሽ እንደተሰጠው የተገለፀ ሲሆን በዚህ ትንኮሳ ወቅት ያሰለፋቸው ያልሠለጠኑ ሕጻናትና ሴቶችን መሆኑም ታውቋል።
ጁንታው ከአካባቢው ሲሸሽ ከ300 በላይ የሕጻናትና የሴቶች አስከሬኖችን በሲኖ ትራክ ጭኖ ወደ መቐለ መፈርጠጡም ታውቋል ብሏል።
ጁንታው በዚህ መልክ የሚያሸሻቸውን የሕጻናትና የሴቶች አስከሬኖች በአንድ መቃብር በመቅበር የጅምላ ግድያ የተፈጸመባቸው መቃብሮች አስመስሎ ለማቅረብ እየተዘጋጀ መሆኑንም የደህንነት ምንጮችን ዋቢ ያደረገው የመረጃ ማጣሪያው መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.