Fana: At a Speed of Life!

ጃፓይጎ በአማራ ክልል ጉዳት ለደረሰባቸው የጤና ተቋማት 12 ሚሊየን ብር የሚገመት ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ጃፓይጎ የተሰኘው ድርጅት በአማራ ክልል በጦርነቱ ጉዳት ለደረሰባቸው የጤና ተቋማት የሚውል 12 ሚሊየን ብር የሚገመት የቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ።

የድርጅቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ወይዘሮ ሸዋ ግርማ ፥ ድርጅታቸው የእናቶችንና የሕጻናትን የጤና አገልግሎት ለማሻሻል ሲሠራ መቆየቱን ተናግረዋል።

አሸባሪው የህወሓት ቡድን በፈፀመው ወረራ ከፍተኛ ጉዳት ለደረሰባቸው የጤና ተቋማት ድጋፉን ማበርከታቸውን ገልጸዋል።

ድርጅቱ ያበረከተው ድጋፍ በደቡብ ወሎ ዞን ለሚገኙ ለአቀስታ አጠቃላይ ሆስፒታል እና ለገነቴ ጤና ጣቢያ እንደሚውል የተገለጸ ሲሆን ፥ ድጋፉ 12 ሚሊየን ብር የሚገመት መሆኑን ሥራ አስኪያጇ ጠቁመዋል።

ድርጅቱ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አስታውቀዋል።

ድጋፉን የተረከቡት የአማራ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር መልካሙ አብቴ በበኩላቸው በወረራው የጤና ተቋማት ላይ ከፍተኛ ውድመት መድረሱን ጠቅሰው፥ ለዓመታት የተገነቡትን ተቋማት ለመመለስ ብዙ ዓመት እንደሚጠይቅ አስረድተዋል።

የጤና ተቋማትን ወደ ነበረቡት ለመመለስ የረጂ ድርጅቶች ሚና ከፍተኛ መሆኑን አመላክተው ፤ ድርጅቱን አመሰግነዋል ፤ ሌሎች ረጅ ድርጅቶችም የጤና ተቋማትን መልሶ ለማቋቋም የሚደረገውን ጥረት እንዲደግፉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በክልሉ ጉዳት የደረሰባቸውን የጤና ተቋማት ወደነበሩበት ለመመለስ ረጅም ጊዜ እንደሚፈጅ መናገራቸውን አሚኮ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.